ምስካየ ሕዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ2015 ዓ.ም የመማር ማስተማር ተግባሩን ብፁዓን አባቶች በተገኙበት በይፋ አስጀመረ!! - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, September 19, 2022

ምስካየ ሕዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ2015 ዓ.ም የመማር ማስተማር ተግባሩን ብፁዓን አባቶች በተገኙበት በይፋ አስጀመረ!!

(መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ) ከአፀደ ሕፃናት እስከ መሰናዶ ትምህርት ለእረጅም ዓመታት እያስተማረ የሚገኘው የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት ብፁዓን አባቶች በተገኙበት የ2015 ዓ.ም የመማር መስተማር መርሐ ግብሩን በይፋ ጀምሯል። በመርሐ ግብሩም ላይ የሩቅ ምሥራቅ ፣ እንግሊዝ ፣ አየርላንድና አካባቢው ሀገራት ሊቀጳጳስና የዓለም የሰላም አምባሳደር ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ፣ የምዕራብ ሐረርጌና አፋር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል። የገዳሙ አስተዳዳሪ መጋቤ ኅሩያን ቆሞስ አባ ኤልያስ በልሁ ለብፁዓን አባቶች የእንኳን ደኅና መጣቹ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የ2014 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደትና አጠቃላይ የትምህርት ቤቱ የሥራ ክንውን በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ወርቁ አሸናፊ አማካኝነ የተቀረበ ሲሆን የ2014 ዓ.ም በ 8ኛ ፣ በ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የወርቅ ሜዳሊያና የሰርተፍኬት ሽልማት እንዲሁም የላቀ የሥራ አፈጻጸም ላደረጉ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የማበረታቻ የሽልማት መርሐ ግብር በብፁዓን አባቶች ተከናውኗል። በተያያዘ ዜናም ከሦስት ዓመታት በላይ በገዳሙ የአብነት ትምህርት ቤት ሥር በሚገኘው የቅዳሴ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ደቀመዛሙርት የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ፕሮቶኮል ክቡር ሊቀ ጉባኤ አባ ኃይሉ እንዳለ አማካኝነት ቀርበው ተመርቀዋል። ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በዕለቱ ባስተላለፉት መልእክት በከፍተኛ የትምህርት ጥራት በውጤት የታጀበ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘውን የትምህርት ተቋሙ በበላይነት የሚመሩትን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ፣ በምሥራቅ አፍሪካ (ኬንያ ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ) አህጉረ ስብከት ፣ የምስካየ ሕዙናን ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስን በአመራራቸው ላስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት ምሥጋና አቅርበዋል። ብፁዕነታቸው አክለውም የጥበብ ሁሉ ምንጭ የሆነውን ልዑል እግዚአብሔርን ጥበብን ፣ ማስተዋልና የፈጠራ ችሎታን እንዲሰጠን በጸሎት መጠየቅ ይገባል ብለው የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሰላም ፣ የውጤትናና የስኬት እንዲሆን ተመኝተዋል ሲል ገዳሙ በፌስቡክ ገጹ አሳውቋል።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages