የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ቅዱስነታቸውን እንኳን ለ፳፻፲፭ ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሰዎ ብለዋል። - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, September 19, 2022

የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ቅዱስነታቸውን እንኳን ለ፳፻፲፭ ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሰዎ ብለዋል።

የማኀበረ ቅዱሳን አመራር አካላት ዛሬ መስከረም ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትን እንኳን ለ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሰዎ ብለዋል፡፡ የማኅበሩ አመራር በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በመገኘት ለቅዱስነታቸው የወንጌለ ዘወርቅ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም የማኅበሩ አመራር አካላት እንኳን አደረሰዎ ለማለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽና ከማኅበሩ ለተበረከተላቸው ስጦታ አመስግነዋል፡፡ ማኅበሩ የሚያከናውናቸው መንፈሳዊ ተግባራት ሁሉ የተሳኩና ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ቃለ በረከትና ቡራኬ ሰጥተዋል።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages