"የካህኑን ቃል እንዳትተው" - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, September 19, 2022

"የካህኑን ቃል እንዳትተው"

‹‹ከዕለታት በአንድ ዕለት እሑድ ቀን አቡነ ሀብተ ማርያም ከቤተ እግዚአብሔር ገብተው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ እንዳስለመዱትም ቃላቸውን ከፍ አድርገው ወንጌልን ሲያነቡ ምራቃቸው ከአፋቸው ወጥቶ ምድር ላይ ቢወድቅባቸው ደንግጠው ስለክብረ ቊርባን በመስቀላቸው ባርከው ምራቃቸውን ከነአፈሩ አንሥተው ጎረሱት፡፡ ጌታችንም በዚህ ጊዜ በሚያስፈራ ግርማ ተገልጦላቸው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ከተቀበሉ በኋላ ጮኸው ወንጌልን ስለማንበባቸው ገሠጻቸውና ‹‹…አሁንም ስለበደልህ ራስህን ለካህን አስመርምረህ እልፍ ስግደት ስገድ› አላቸው፡፡ ይህንንም ካዘዛቸው በኋላ ተሰወራቸው፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያም ‹‹በስንፍናየ ምክንያት ፈጣሪዬን አሰሳዘንኩት›› ብለው ጽኑ ለቅሶን እያለቀሱ ተነሥተው ከቄሱ ዘንድ ሔደው የሠሩትን ኃጢአት ሁሉ አስተካክለው ለቄሱ ተናገሩ፡፡ ቄሱም አባታችንን ‹በደሉ ቀላል ነውና ሦስት ጊዜ ስገድ›› አላቸው፡፡ እርሳቸውም እሽ ብለው ከወጡ በኋላ ‹‹ጌታዬ ‹እልፍ ስገድ› ብሎ እልፍ ስግደት አዝዞኝ ነበር ቄሱ ደግሞ ሦስት ስግደት ሰጠኝ፣ ምን ላድርግ?› ብለው እየተጨነቁ ሣለ ዳግመኛ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦላቸው ‹የካህኑን ቃል እንዳትተው ለራስህ ዕወቅ፣ ካህኑ ከአዘዘህ በላይ ሌላ አትጨምር› አላቸው፡፡›› ክብረ ክህነት እስከምን ድረስ እንደሆነ ልብ ይሏል! (ገድለ አቡነ ሀብተ ማርያም ገጽ 93-95)

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages