የ የኔታ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ መምህር ይባቤ በላይ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, September 15, 2022

የ የኔታ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ መምህር ይባቤ በላይ

ከ79 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ወንበር ዘርግተው ጉባኤ ተክለው ለ36ዓመት ቅኔና ቅዱሳት መጻህፍት ትርጓሜ ያስተማሩ አሁንም በማስተማር የሚገኙ በርካታ ደቀመዛሙርት ያስመረቁ የቅኔና የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ መምህር የክብረ ደናግል ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም መሰራችና አስተዳዳሪ ጫካ መንጥረው ምድረ በዳውን አቅንተው ጋራ ሸንተረሩን ገነት አሰመስለው የሚኖሩ ከሰው እጅ ሳይጠብቁ በልማት የሚተዳደሩ በጀሯቸው ትርጓሜ እየሰሙ በእጃቸው ዶማ ይዘው የሚቆፍሩአይምሯቸውንም እጃቸውንም የሚያሰሩ የኔታ ጀሯቸው ትርጓሜ ይሰማል አንደበታቸው ምስጢር ያፈልቃል የተሰወረውን ይገልጣል የረቀቀውን ያጎላል የተሳሳተውን ያርማል የጠመመውን ያቀናል እጃቸው ደግሞ ዶማ ይዞ ይቆፍራል እኛ ቀጭ ብለን ትርጓሜ እንማራለን እሳቸው በአንደበታቸው በእጃቸው ሁለት ስራ ይሰራሉ ይህ ከሌሎች መምህራን ለየት የሚያደርጋቸው ነው እረፍት የማያውቁ እንኳን እረፍት እግዚአብሔር በሚያቀው የእንቅልፍ ስዓት የሌላቸው ትርጓሜ ሲያስተምሩ ቆይተው ሲጨርሱ የቅኔው ተማሪ ይተካል ቅኔ አስነግረው ሲጨርሱ አባታዊ ምክር ፈልገው ከተለያየ አቅጣጫ የመጡ እንጎዶችን ይመክራሉ ታመው የሄዱትን እንዲጠመቁ ያደርጋሉ ተጣልተው የሄዱትን ያስታርቃሉ ማህበራዊ ችግሮችን በተሰጣቸው ጸጋ ይፈታሉ ስንፍና የተጠናወታቸውን ልማት ተግባረ እድ ያስተምራሉ ዶክተሩ ሲሄድ የሙያው ባለቤት ሆነው ይገኛሉ ፖለቲከኛው ሲሄድ ሀገር የምትድንበትን አቅጣጫ ያሳዩታል የግብርና ባለሙያው ሲሄድ እሱ በወረቀት የተማረውን የሚያውቀውን እሳቸው በተግባር ያሳዩታል ሁሉንም እንደየሙያቸው የልባቸውን ሲነግሯቸው ከየት አገኙት ከየት ተማሩት እያሉ ራሳቸውን እየነቀነቁ ከንፈራቸውን እየመጠጡ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ጭነው ወደ እየመጡበት ይመለሳሉ ሰለእርሳቸው እንዲህ በቀላሉ መናገር አይታሰብም አይሞከርም የሚያውቅ ያውቀዋል በፌስቡክ መንደር ያልተዘመረላቸው የፌስቡኩ ትውልድ የማያውቃቸው በፌስቡክ ሰፈር ፎቷቸው የማይለጠፍ ፌስቡኩ የማያውቃቸው እሳቸወም ሊያውቁት የማይፈልጉ የማህበራዊ ሚዲያው ትውለድ ምርጦቹ ተሰውረውበታል ምክንያቱም የእየለቱን እንቅስቃሲያቸውን አይጽፉም ኢንተርኔት አይጠቀሙም ማስታወቂያ እንዲነገርላቸው አይፈልጉም ፎቷቸውን በእየቀኑ አይለቁም በእየቀኑ ያፈራሉ ፍሬያቸው ደግሞ እንዲታይ አይፈልጉም ማህበራዊ ሚዲያውን በእየቀኑ አያጨናንቁትም ነገር ግን ፌስቡኩን ቀድመውት የሄዱ የተሻገሩ እንዳልኳችሁ ማህበራዊ ሚዲያው ብዙ ባያውቃቸውም በታላላቅ ሊቃውንት በብጹአን አባቶች በምሁራን በከፍተኛ የክልልም ሆነ የፈደራል ሚንስትሮች /ባለስልጣናት እንዲሁም በበሳል ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ እውቅና የተቸራቸው ከክልሉ ፕሬዚዳንት ከፌዴራል በልማት አርበኝነታቸው ሜዳልያ በተደጋጋሚ የተበረከተላቸው መጽሐፋዊ ቅኔያዊ አባታዊ ልማታዊ ብቻ ብዙ ሃብተ ጸጋ ያላቸው ሊቅ ናቸው ሐሰተኛ ባህታውያን ሐሰተኛ አጥማቂዎች እንደ ጦር የሚፈሯቸው ሐሰተኛ አጥማቂዎች እንደ ዛሬ በፌስቡክ አደባባይ ጦርነት ሳይበረታባቸው ቅድመው ፊት ለፊት የተጋፈጧቸው አሁንም በመዋጋት የሚገኙ በዚህ ውጊያም ብዙ ነፍሳትን ያተረፉ የጻድቁ አቡነ ተከሰተ ብርሃንን አራያ በመከተል በአዲስ ሸክላ አማካኝነት የምትመለክ ሙላድ የምትባል የዛር ውላጅ ከብዙ ገበሬ ቤት ተማሪዎቻቸውን ይዘው ያስወገዱ ጣኦታትን የሰበሩ የዲማው ሊቅ የነበሩ የአለቃ ማርቆስ ደቀመዝሙር የትርጓሜ መምህርየ አስተማሪየ የኔታ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ መምህር ይባቤ በላይ እንኳን አደረስዎ እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገርዎ የኔታ ይኑሩልኝ እረጅም እድሜ ተመኘሁ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages