ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, September 15, 2022

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቅዱስነታቸው የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ላይ ካስተላለፏቸው መልዕክቶች የተወሰደ‼ መስከረም ፪ቀን፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም አዲስአበባ -ኢትዮጵያ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሪ የሚሆኗት እውነትና ብርሃን ናቸው። በዚህ ወቅት ያ ብርሃን እየደደበዘዘና የቤተ ክርስቲያን ክብር እየቀነሰ መጥቷል። በአዲሱ ዓመት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን"'መጥዎተ ርእስ "" ራስን መሥጠት"ያስፈልጋል። የቤተ ክርስቲያንን ክብር ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ በአዲሱ ዘመን ነቅፈው ለነቃፊ ከሚያሰጡን ተግባራት ራሳችንን ማራቅ፤ ሃይማኖቱና ፖለቲካ ተቀላቅሎበት ግራ የተጋባ ካለም ለሃይማኖቱ ብቻ ግንባር ቀደም ጠበቃ በመሆን ሃይማኖቱንና ቤተክርስቲያንን ጠብቆ ማስጠበቅ የሚችልበትን ሥራ መስራት ይኖርበታል። አዲሱ ዓመት ከፖለቲካ ጋር ከተቀላቀሉ ጉዳዮች ርቀን፤ ሴራ፣አድማ፣ተንኮልና ምቀኝነትን የመሳሰሉ ተግባራት ሁሉ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ተጠርጎ ወጥቶ በምትኩ ሰላምና ፍቅር ነግሶ በአንድነት ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የምንረባረብበት ጊዜ መሆን ይገባዋል። የአብነት ትምህርት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወሳኝ ምዕራፍ በመሆኑ የአብነት መምህራን በሥራ እጦት የሚንገላቱበት ጊዜ አብቅቶ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል የሚደረጉ ቅጥሮች ለአብነት መምህራን ቅድሚያ የሚሰጡ መሆን ይገባቸዋል። ሃይማኖትን ከፖለቲካ ፖለቲካን ከሃይማኖት መቀላቀል አይቻልም። እኛ የቤተክርስቲያን ወታደሮች ነን፤ ከዛሬ ጀምሮ በዘር በጎሣ በነገድ በክፋት በሴራ ቤተክርስቲያንዋን ዝቅ ማድረግ አይቻልም።ቤተክርስቲያን ትናትም ዛሬም ታላቅ ናት ነገም ታላቅ ትሆናለች ፤

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages