የመናፍቃን ማንነት ሲገለጥ (በዝግታ ቀስ በቀስ የስውሩን ዓለም ገዢ ማለማመ) - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, September 15, 2022

የመናፍቃን ማንነት ሲገለጥ (በዝግታ ቀስ በቀስ የስውሩን ዓለም ገዢ ማለማመ)


የመናፍቃን ማንነት ሲገለጥ 

 በመጀርያ በሁሉም ነገር ውስጥ ይሰማራሉ።
መዝናኛ፣
ኢኮኖሚ፣
ትምህርት፣
ሃይማኖት ውስጥ ተመሳስለው ይሰርፃሉ። ለነዋይ እና ለዝና ስስ ልብ ያላቸውን ጥሩ ዕቃ ያደርጋሉ፣

ክርስቶስን ከመለኮታዊ ማዕረግ በአስተምሮት ዶክትሪናቸው ያወርዱታል። ታናሽ አምላክ አድርገው በተከታዮቻቸው ጭንቅላት ውስጥ ይቀርፃሉ
ተለማኙን ለማኝ ፣
ተማላጁን አማላጅ፣
ፈራጁን አሳሳቢ አድርገህ የአብርሐም የይስሐቅን አምላክ ከአብርሃም እና ከይስሐቅ ክብር ጋር እኩል ያስቀምጣሉ።

ቀጠል ያደርጉ እና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልክ እንደ አቻ ጓደኛ
የሱሴ፣
የእኔ ማር፣
ፍቅሬ የሚል ቅጥያ የበታች ስሞችን አስታቅፈው የቆሎ ጓደኛ ያክል ህዝቡን ያለማምዱታል::

አሁንም ይቀጥሉ እና ተከታዮችህ
የእዚህን ዓለም ቁስ፣
ሐብት፣
ደስታ፣
ተድላ፣
ምቾት እና ገዢነት ብቻ ናፍቀው ዘመናቸው እንዲያልቅ በራዕይ በትንቢት አስታከህ የሐሰተኛ ነብያትን መጫወቻ ያደርጉታል።

ህግ አልባ፣
ስርዓት የለሽ፣
ገድብ የሌለው ትውልድ እንዲፈጠር ከመጽሐፍ ቅዱስ አንቀጽ መሐል ያለን አንድ ቃል ያለአውዱ  መዘው የስብከት ርዕስ አድርገው ያስፈነድቃሉ።
መንፈሳዊነት እና ዓለማዊነት እስኪደበላለቅ ድረስ መዝሙር እና ስብከቶች  የጩኸት የእሩምታ የዳንስ ትዕይንት መገለጫ ይሆናሉ ።

ከዓለም የሆነ ሁሉ የምታመልከው ቤት ውስጥ ታገኛለህ።

የሶዶም ህግ፣ የፈርዖን ትዕዛዝ አሰራር ይሆናል ።

"ምን ችግር አለው"፣ "ምን ታካብዳለህ" የሚል ትውልድ እንደ አሸን ይበዛል።

የሃይማኖት የስብዕና ህግጋት፣
ማህበራዊ ግብረ ገብነት፣
ሰዋዊ የሞራል ከፍታዎች እንዲወድሙ ይደረጋሉ።

ይህን ጊዜ የጨለማውን ዓለም ገዢ ምልክት ያስተዋውቃሉ።
በስውር የሚሰሩትን ቀስ በቀስ በግልጥ ያጮልቃሉ።

ልብ አምላክ ዳዊት በመዝሙር መጽሐፍ “አያውቁም፥ አያስተውሉም፤ በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፤  መዝ82፥5" ያለውን ቃል ማስታወስ ግድ የሚልበት ዘመን ላይ ደርሰናል።


No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages