የ፳፻፲፭ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በተመለከተ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ አቅጣጫዎች አስቀመጠ‼ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, September 15, 2022

የ፳፻፲፭ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በተመለከተ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ አቅጣጫዎች አስቀመጠ‼

የ፳፻፲፭ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በተመለከተ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ አቅጣጫዎች አስቀመጠ‼ በብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ርዕሰ መንበርነት የሚመራው የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባዔ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የ፳፻፲፭ ዓ.ም #የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ግምገማ ያደረገ ሲሆን የሚከተሉትንም አቅጣጫዎች አስቀምጧል። ፩ኛ የበዓል አከባበሩ ሥራ በልዩ ትኩረትና ውጤት ሊያመጣ በሚችል አግባብ መከናወን የሚገባው ስለሆነ ንዑሳን ኮሚቴዎች ቀሪ ሥራዎቻቸውን ትኩረት ሰጥተው እንዲያከናውኑ፤ ፪ኛ በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ ፣ደማቅና የተሳካ በዓል ሆኖ መከበር ይችል ዘንድ በጸጥታው ዘርፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመናበብ በጋራ በሚቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እንዲከናወን፤
፫ኛ ከበዓሉ ጋር የማይሄዱና ሁከት ቀስቃሽ ጥቅሶችን በመጠቀም አግባብነት የሌለው መልዕክቶች እንዳይተላለፉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ መሰረት ያደረገ ሥራ በሁሉም ንዑሳን ኮሚቴዎች አማካኝነት በልዩ ትኩረት እንዲሰራ፤ ፬ኛ ሁሉም የበዓሉ ተሣታፊዎች ማለትም ካህናት ፣ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ም ዕመናንና ምዕመናት ከጸጥታ አካላት ጋር መተባበርና በመናበብ እንዲሠሩ፣ በዚህም በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ፤ ፭ኛ በቲሸርቶችና በባነሮች ላይ የሚተላለፉ መልእክቶች ሁከት ቀስቃሽ እንዳይሆኑ፣የፌዴራል ወይም የቤተክርስቲያናችን አርማ ካለበት ባንዲራ ውጪ በዓሉ ላይ ይዞ መውጣት በፍጹም የተከለከለ መሆኑን ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች እንዲያውቁት የማድረግ ሥራ ከበዓሉ ቀደም ብሎ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በኩል እንዲገለጽ፤ ፮ኛ የጸጥታ አካላት በዓሉ በሰላም ተከብሮ ማለፍ ይችል ዘንድ የሚያከናውኑትን የፍተሻ ሥራ ፍጹም ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በተሞላበት ጨዋነት መተባበር እንደሚገባ እስከ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ድረስ መልዕክቱ እንዲተላለፍ እንዲደግ፤ ፯ኛ በበዓሉ ዕለት በሚዲያ ወይም በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፉ መንፈሳዊ መልዕክቶች አስቀድመው በተለዩና በተቋም ደረጃ በሚታወቁ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አማካኝነት ብቻ እንዲተላለፍ እንዲደረግ፤ ፰ኛ የህትመት ውጤቶችን በተመለከተ ቤተክርስቲያናችን በማዕከል ደረጃ ካሳተመቻቸው መጽሔትና ብሮሸር ውጪ ምንም አይነት የህትመት ውጤት እንዳይሰራጭ ፤ ፱ኛ ደመራው በጥንቃቄና በሰዓቱ እንዲደመርና ባዕድ ከሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች የጸዳ መሆኑን አስቀድሞ የማረጋገጥ ሥራ እንዲከናወን፤ ፲ኛ የክብር እንግዶች መግቢያ ባጅ፣ የመኪና ይለፍና ሌሎች መስቀል አደባባይ የሚታደሙ ሰዎች መግቢያዎችን በተመለከተ ከወትሮው በተለየ ጥንቃቄ ተሰርቶ በአግባቡ እንዲሰራጭ እንዲደረግ፤ መስከረም ፭/፳፻፲፭ ዓ/ም ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages