መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ፵ ኛ ቀን መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎት ታስቦ ዋለ። - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Sunday, October 16, 2022

መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ፵ ኛ ቀን መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎት ታስቦ ዋለ።

መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ፵ ኛ ቀን መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎት ታስቦ ዋለ።

ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም


አንጋፋው ሊቅና ጋዜጠኛ የመጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ፵ ኛ ቀን መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል 
 
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመ/ፓ/ጠ/ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊዲንና የስካንዲኔቪያ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፤ ቤተሰቦቻቸውናወዳጆቻቸው በተገኙበት በጸሎት ታስቧል። 
 
በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ስለ ሊቁ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ምስክርነት ትምህርትና ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል:: መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በድሮው አጠራር በወሎ ጠቅላይ ግዛት የጁ አውራጃ ሐብሩ ወረዳ ልዩ ስሙ ዳኅና ማርያም ቤተክርስቲያን አጥቢያ ከታወቁት ሊቅ አባታቸው አለቃ ፈታሒ ወልደማርያምና ከእናታቸው ወይዘሮ አበበች ያዘው በ1928 ዓ/ም ነበር የተወለዱት። 
 
ከልጅነታቸው ጀምሮ የአብነት ትምሕርትን ከልዩ ልዩ ሊቃውንት የተማሩት መጋቤ ምሥጣር ወልደሩፋኤል ፈታሒ ስለ ቅኔ ትምህርት ስፋትና ጥልቀት ከታወቁ መምህራን የቅኔን ይትበሀልና ሙያ ጠንቅቀው የተማሩ ሲሆን በቅኔ ሙያቸውም አንቱታን አትርፈዋል።
 
ከታወቁበት የቅኔ ሙያ በተጨማሪ ወደ ትርጓሜ መጻሕፍት ትምህርት በማሳደግ በርካታ ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተመርቀው ወደወጡበት ዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ቤት ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም የካህናት ማሰልጠኛ ገዳም ገብተው የቅዳሴ ማርያምን ትርጓሜ አጠናቀው ተምረዋል።
 
እንዲሁም በአሰቦት ደብረ ወግ ቅድስት ሥላሴ ገዳም ቅኔ በሚማሩበትና ተመርቀው በሚወጡበት ጊዜ ማታ ማታ ቅኔ እየተማሩ ቀን ቀን ከገዳሙ መጻሕፍተ ብሉያት ትርጓሜ መምህር የመጽሐፈ ነገሥትን ትርጓሜ በማጠናቀቅ ተምረዋል፡፡ 
 
ከዚያ በመቀጠልም በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ አዳሪ ትምህርት ቤት በአዳሪ ተማሪነት ገብተው የአንደኛ ደረጃና ዘመናዊ ትምህርት ከመማር ጋር የመጻሕፍተ ሐዲሳትን ትርጓሜ አጠናቅቀው ተምረዋል፡፡ 
 
መንፈሳዊና ዘመናዊ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከጨረሱ በኋላ ባላቸው መንፈሳዊና ዘመናዊ ዕውቀት ወደ ሥራ ዓለም ለመግባት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተመድበው በኢሉባር ሀገረ ስብከት በሰባኬ ወንጌልነት ተመድበው ለሁለት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመዛወር፡፡ 
 
ባላቸው የቅኔና የሥነ ጽሑፍ ልዩ ችሎታ ተመርጠው ጥር 9 ቀን 1958 ዓ.ም ጀምሮ ከቤተ ክርስቲያኒቱ እየተዘጋጀ ‹‹በማስታወቂያና መርሐ ብሔር ሚኒስትር›› በሬዲዮ ይሰጥ ለነበረው ትምህርት አዘጋጅና የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ሪፖርተር በመሆን ሲአገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ታህሣሥ 2 ቀን 1963 ዓ.ም ጀምሮ የሥነ-ጽሑፍ ክፍል ሓላፊና የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ አዘጋጅ ሆነው ሠርተዋል ;ታህሣሥ 4 ቀን 1967 ዓ.ም ጀምሮ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ አዘጋጅ በመሆን እስከ ዕለት ኅልፈታቸው ሠርተዋል፡፡ 
 
መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በረጅሙ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎታቸው ዘመን በአሜሪካን፣ በራሽያ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በናይሮቢ፣ በግብጽ፣ በሶሪያ፣ በሊባኖስ የዓረብ ኢምሬቶችን በመላ ሀገራችን በሚገኙ አህጉረ ስብከት በአካል በመገኘት ሰፊ መንፈሳዊ አገልግሎት የሰጡ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ነበሩ፡፡
 
መጋቤ ምሥጢር ወሩፋኤል ፈታሒ ያላቸውን ከፍተኛ የሥነ ጽሑፍ ችሎታ በኃላፊነት በሚያዘጋጁትዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ አማካኝነት ቃለ እግዚአብሔርን አስተምረውናል፣ የቤተ ክርስቲያቱን መልእክት አስተላፈዋል ጠንካራገላጭና ተቋም ተኮር ምክረ ሐሳብ በማቅረብም ለቤተ ክርስቲያናቸው በሙያቸው ጥብቅና የቆሙ ሊቅ ነበሩ፡፡© EOTC TV

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages