ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የ ፵፩ኛው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤን የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተዛውረው ተመለከቱ። - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Sunday, October 16, 2022

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የ ፵፩ኛው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤን የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተዛውረው ተመለከቱ።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የ ፵፩ኛው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤን የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተዛውረው ተመለከቱ።


ጥቅምት ፮ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም

አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
***************
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤን በስኬት ማከናወን የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ መከናወኑን ተዛውረው ተመለከቱ።
ብፁዕነታቸው የጉባኤው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማለትም የአዳራሽ ዝግጅትና የዲኮር ሥራዎች፣የህትመትና የጽሕፈት መሳሪዎች ዝግጅት፣ የሳውን ሲስተም ዝግጅትና የተሳታፊዎች የመግቢያ ባጅ ሥርጭት በሚገባ መከናወኑና አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በሚገባ መጠናቀቃቸውን ተመልክተዋል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ እያንዳንዱ ሥራ በተያዘለት ዕቅድ መሰረት መከናወኑን የማረጋገጥ ሥራን በሚያከናውኑበት ወቅት የሰጧቸው መመሪያዎችና ያደረጉት የቅርብ ክትትል አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ በሚገባ እንዲጠናቀቅ አስችሏል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጉባኤው በስኬት እንዲካሔድ ለማድረግ የሚሰራው ሥራ ውጤታማ እንዲሆን ከማድረጋቸውም ባሻገር ጉባኤው ከሪፖርት ማድመጥና ከፋይናንሳዊ ሪፖርቶች ትኩረት መስጠት ባለፈ የውይይትና የመፍትሔ ማፍለቂያ ጉባኤ መሆን ይችል ዘንድ ጥልቅ ውይይት የሚደረግበትን አሰራር የዘረጉ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ያደርጋቸዋል።
የዘንድሮ ጉባኤ የቤተክርስቲያናችን ውሳኔ ሰጪ ጉባኤ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ጉባኤ በመሆኑ በሰለጠነ፣ በሰከነና ብስለት በተሞላበት መንፈስ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የተፈጠረለትን መልካም እድል በሚገባ ተጠቅሞ ቀጣይ የቤተክርስቲያናችንን አቅጣጫ ጭምር ማመላከት ይኖርበታል።

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages