በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት 830 በላይ አዳዲስ አማኞች መጠመቃቸውን ተገለጸ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Sunday, October 16, 2022

በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት 830 በላይ አዳዲስ አማኞች መጠመቃቸውን ተገለጸ

 

በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት 830 በላይ አዳዲስ አማኞች መጠመቃቸውን ተገለጸ:: 

ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም

 

አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
**************
በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከስምንት መቶ ሠላሳ በላይ አዳዲስ አማኞች እንደተጠመቁ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሱን ወንጌል በማስተማርና ያመኑትንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማጥመቅ የእግዚአብሔር ልጆች የመንግሥተ ሰማይ ወራሾች ማድረግ ሁነኛ ዓላማዋ ሲሆን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ግን ከዚህ በተጨማሪ የጎሳ መሪዎች ሸምጋይና ለጠብ አስታራቂ መሆኗን ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በዓውደ ምሕረት የጎሳ መሪዎችን ማስታረቃቸውን ተገልጿል።
በዚህ ዓመት በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከመስከረም ፳፯_ ጥቅምት ፩/፳፻፲፭ ዓ/ም ባሉ አምስት ቀናት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መሪነት በዳሰነኝ ና በደቡብ አሪ አካባቢዎች በደሳሳ ጎጆ ይገለገሉ ለነበሩ አማኞች የሚያገለግል ቤተ ክርስቲያን ከመባረክ ባለፈ አዲስ አማኞችንም የማጥመቅ አገልግሎት መከናወኑን አስረድተዋል።
ብፁዕነታቸው አክለው ወደ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የተጨመሩት አማኞች ከተጠመቁ በኋላም የማጽናት ትምህርት እንደሚሰጣቸውም ገልጸው
በዚህ አካባቢ በተባበረ መልኩ ቢሠራበት ብዙ ነፍሳትን ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲጨመሩ ማድረግ እንደሚቻል ተናግረዋል ተብሏል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው በዚህ ሰዎችን የመንግሥተ ሰማይ ዜጋ የማድረግ ጉዞን ሁሉም አካል መደገፍ እንደሚገባው አስታውሰው በተለይ የአከባቢው ማኅበረሰብ በሥጋዊ የኑሮ ድክመት ምክንያት ለነጣቂ ተኩላ ራት እንዳይሆኑ የሚስተዋሉ የአብነት ትምህርት እጦት ፣የውኃ፣ የጤናና መሰል ችግሮችን በተቻለ መጠን እንደ ቤተ ክርስቲያን መፍትሔለመስጠት ይቻል ዘንድ ዋጋ አገኛለሁ የሚል ክርስቲያን ሁሉ ሊያግዝ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል ሲል የEOTC TV ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages