የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለ፳፻ ፲ ወ፭ በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚያ አንድ ቢልየን ዘጠና ሚልየን አጸደቀ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Wednesday, November 2, 2022

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለ፳፻ ፲ ወ፭ በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚያ አንድ ቢልየን ዘጠና ሚልየን አጸደቀ

 


የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለ፳፻ ፲ ወ፭ በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚያ አንድ ቢልየን ዘጠና ሚልየን አንድ መቶ ሰባ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሳንቲም አጸደቀ።

ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻ ፲ ወ፭ ዓ.ም

አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባካሔደው መደበኛ ጉባኤው ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፤ የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም በጀትንም አጽድቋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤው በዛሬው ዕለት ከተወያየባቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ በቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ተጠንቶ በቀረበውና የቤተክርስቲያን አእምሯዊ ሀብቶችና ንብረቶች ባለቤትነትና ጥበቃ ጉዳይን የሚዳስሰውን ጥናት የሚመለከት ሲሆን የጥናት ሰነዱ በመምሪያው ኃላፊና በተቋቋመው አጥኚ ኮሚቴ በኩል ቀርቦ ምልአተ ጉባኤው ውይይት አድርጎበታል። በጥናቱ አስፈላጊነትና አተገባበር ዙሪያም ውሳኔ አስተላልፏል።በሌላ በኩል ቤተክርስቲያን በአገር አቀፍ ደረጃ በምታበረክተው የቱሪዝም አቅርቦትና ተጠቃሚነት ዙሪያ ለወደፊቱ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር መወያየት እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጧል።
በመጨረሻም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጀትና ሒሳብ መምሪያ ያቀረበውንና በ፳፻ ፲ ወ፭ዓ/ም በጀት ለማከናወን ለታቀዱ ዕቅዶች ማስፈጸሚያ የሚሆን አንድ ቢልየን ዘጠና ሚልየን አንድ መቶ ሰባ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሳንቲም በማጽደቅ የእለቱን ጉባኤ አጠናቋል።የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በነገው ዕለት ጉባኤው በቀሪ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል።
 
መረጅውን ያገኘነው ከEOTC TV ነው።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages