ምሥጢረ ዕለተ አርብ {ስቅለት } - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 14, 2023

ምሥጢረ ዕለተ አርብ {ስቅለት }




👉 እለተ አርብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት ቀን ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው ስቃይና መከራ ለዓይን የሚዘግንኑ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ከባድ ቀንን ለእኔና ለእናንተ ፍቅር ሲል አሳልፏል ።
ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፋን አልከፈተም ። ኢሳ ~ 53:7
13 ቱ ~ ህማማተ መሰቀል
1. እራሱን በዘንግ ተመታ ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው እራሱን መቱት ። ማቴ ~27:30
2. በጥፊ ተመታ ፦በጥፊም ይመቱት ነበር ። ዮሐ ~19፥4
3. ምራቅ ተፋበት ፦ተፋበትም መቃውንም ይዘው እራሱን መቱት ።
ማቴ ~ 27፥30
4.የሾክ አክሊል ጎንጉነው በእራሱ ላይ አቀደጂት ማቴ ~27፥29
5. መራራ ሀሞት አጠጡት ፦ በሀሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት ፤ ቀምሶም ሊጠጦው አልወደደም ። ማቴ ~ 27 ፥ 34
6. ጀርባውን መገረፍ ፦ በዚያም ጊዜም ጰላጦሰ እየሱስን ይዞ ገርፈው ።
ዮሐ ~19፥1
7. ጎኑን በጦር መወጋት ፦ ነገር ግን ከጭፈራዎቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ወድያውም ደምና ውኃ ወጣ ። ዮሐ ~19 ፥34
8. ወደ ኃላ መታሰሩ ፦ የሾለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሌሎችም እየሱስን ይዘው አሰሩት ። ዮሐ ~18 ፥ 12
9. ሳዶር
10. አላዶር
11. ዳናት
12. አዴራ
13. ሮዳሰ
5ቱ ቅንዋተ መሰቀል ችንክሮች ሳዶር ፣ አላዶር ፣ ዳናት ፣አዴራ ፣ ሮዳሰ ይባላሉ ።
1. ሰዶር ~ማለት ቀኝ እጁ የተቸነከረበት
2. አላዶር ~ ማለት ግራ እጁ የተቸነከረበት
3. ዳናት ~ማለት እግሮቹ ነተቸነከረበት
4. አዴራ ~ማለት ደረቱን የተቸነከረበት
5. ሮዳሰ ~ማለት ከወገቡ {እብርቱ } አጣብቆ እንዲይዝ የተቸነከረበት

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ የተፈፀሙ 7ቱ ተአምራት
1. ጸሀይ ጨለመች
2. ጨረቃ ደም ለበሰች
3. ከዋክብት ብርሃናቸውን ነሱ
4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከሁለት ተከፈለ
5. አለቶች ተሰነጣጠቄ
6. መቃብራን ተከፈቱ
7. የሞቱት ተነሱ
ክብርና ምሥጋና አምልኮትና ውዳሴ ስግደት ዝማሪ ይድረስ ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ
አሜን።
አቤቱ አምላካችን ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አሰብን

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages