ጸሎተ ሐሙስ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 14, 2023

ጸሎተ ሐሙስበዚህች ዕለት ጌታችን በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡

በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ ይህ ዕለት #የምሥጢር_ቀንም ይባላል፡
†በመብል ያጣነውን ክብር በመብል የተመለሰልን ዕለት በመሆኑ ጌታችን በሰጠን ሥልጣን ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር በማብቃቱ #የነጻነት_ሐሙስም ጭምር ይባላል ፡፡
† በዚህ ዕለትም ሌላ የተፈጸመው ተግባር #ሕጽበተ_እግር ነው፡፡ ወንጌሉ «፡ተነሣ፡ልብሱንም፡አኖረ፥ማበሻም፡ጨርቅ፡ወስዶ፡ታጠቀ፤
፤በዃላም፡በመታጠቢያው፡ውሃ፡ጨመረ፥የደቀ፡መዛሙርቱንም፡እግር፡ሊያጥብና፡በታጠቀበትም፡ማበሻ፡ጨርቅ፡ሊያ ብስ፡ዠመረ።
፤ወደ፡ስምዖን፡ጴጥሮስም፡መጣ፤ርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡የእኔን፡እግር፡ታጥባለኽን፧አለው።
፤ኢየሱስም፡መልሶ፦እኔ፡የማደርገውን፡አንተ፡አኹን፡አታውቅም፥በዃላ፡ግን፡ታስተውለዋለኽ፡አለው።
፤ጴጥሮስም፦የእኔን፡እግር፡ለዘለዓለም፡አታጥብም፡አለው።ኢየሱስም፦ካላጠብኹኽ፥ከእኔ፡ጋራ፡ዕድል፡የለኽም ፡ብሎ፡መለሰለት።
፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፦ጌታ፡ሆይ፥እጄንና፡ራሴን፡ደግሞ፡እንጂ፡እግሬን፡ብቻ፡አይደለም፡አለው።
፤ኢየሱስም፦የታጠበ፡እግሩን፡ከመታጠብ፡በቀር፡ሌላ፡አያስፈልገውም፥ዅለንተናው፡ግን፡ንጹሕ፡ነው፤እናንተ ም፡ንጹሓን፡ናችኹ፥ነገር፡ግን፥ዅላችኹ፡አይደላችኹም፡አለው።
፤አሳልፎ፡የሚሰጠውን፡ያውቅ፡ነበርና፤ስለዚህ፦ዅላችኹ፡ንጹሓን፡አይደላችኹም፡አለው።
፤እግራቸውንም፡ዐጥቦ፡ልብሱንም፡አንሥቶ፡ዳግመኛ፡ተቀመጠ፥እንዲህም፡አላቸው፦ያደረግኹላችኹን፡ታስተውላ ላችኹን፧ >>ዮሐ 13 ፥ 1-10
በቃል ያስተማረውን ትኅትና በተግባር ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሮል፡፡ “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሁት ነኝና” እንዲል /ማቴ. 11፥29/፡፡ ይህንም ሲፈጽም አሳልፎ ሊሰጠው ያለውን የአስቆሮቱን ይሁዳ አለየውም፡፡
† በዚህ ዕለት ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጠው ተናገረ በዚህም ማንነቱን ጭምር ለይቶ ነገራቸው “እጁን በወጭቱ ያጠለቀው እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ነው”
† የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ማደሩ #ጸሎተ_ሐሙስ ለመባሉ ምክንያት ነው ፤ /ማቴ.26፥36-46፣ ዮሐ.17/በዚች ዕለት ጌታችን በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡
በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ ይህ ዕለት የምሥጢር ቀንም ይባላል፡፡
በመብል ያጣውን ክብር በመብል የመለሰበት ዕለት በመሆኑ ጌታችን በሰጠን ሥልጣን ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር በማብቃቱ #የነጻነት_ሐሙስም ጭምር ይባላል ፡፡

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages