የምክክር መድረክ ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, June 30, 2023

የምክክር መድረክ ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው

 የመጪዉ ዐሥርት ዓመታት የመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት ግቦች ዙርያ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው።

ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በመሪ ዕቅድ መምሪያ አሰናጅነት "ኑ የእግዚአብሔርን ቤት በጋራ እንሥራ" በሚል ርዕስ የመጪዉ ዐሥርት ዓመታት በመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት ግቦች ዙርያ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው።
በመድረኩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የመጪዉ ዐሥርት ዓመታት የመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት / ከ 2016 ዓ.ም - 2025ዓ.ም/ Orthodox Spiritual and Sustainable Development Goals (OS-SDG) ዙሪያ በባለሙያዎች ማብራሪያ ቀርቧል።






ምንጭ፤ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages