ለተመረጡ 5 በጎ አድራጎት ድርጅቶች የአንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ ብር የገንዘብ እርዳታ ተደረገ !
ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መታሠቢያ ድርጅት ለኢየሩሳሌም ለተመረጡ 5 በጎ አድራጎት ድርጅቶች የገንዘብ እርዳታ አደረገ።
ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገው የእርዳታ ልገሳ መርሐ ግብር የድርጅቱ የቦርድ አባላት በተገኙበት ለበጎ አድራጎት ማኀበራቱ ለእያንዳንዳቸው 280,000/ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር/ በድምሩ 1,400,000/አንድ ሚሊዮን 4 መቶ ሺ/ ብር ወጪ በማድረግ ነው እርዳታ የተደረገው። እርዳታ የተደረገላቸው ተቋማትም ጌርጌሴኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ፣ የወደቁት አንሱ በጎ አድራጎት ፣ ኅብረት ለበጎ በጎ አድራጎት ፣ ኪዳነ ምሕረት የተማሪዎች ራስ አገዝ ማኅበር እና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለሚገኝ የበጎ አድራጎት ተቋም መሆናቸው ታውቋል።
ምንጭ፤ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
No comments:
Post a Comment