በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች አስክሬን ተሸኘ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, February 24, 2024

በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች አስክሬን ተሸኘ

 በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች አስክሬን ተረሽነው ከተቀበሩበት ከጊዳ ተክለሃይማኖት አካባቢ ተነስቶ በገዳሙ በክብር ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጸመ።++++++++++++++++++++++++++++++++
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ ዐራት አባቶችን መግደሉን ይታወቃል፡፡
ሰኞ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት በታጣቂዎቹ የተገደሉት የገዳሙ መጋቢ አባ ተክለማርያም ዐሥራትን የገዳሙ ጸሐፊ፣ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን ፣የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ እና በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም የተባሉት የገዳሙ የሥራ ሓላፊዎች ናቸው።
በስልክ የገለጹት አንድ የገዳሙ የሥራ ኃላፊ በግፍ የተገደሉት አባቶች አስክሬን ተረሽነው ከተቀበሩበት በረሀማው ከጊዳ ተክለሃይማኖት አካባቢ ተነስቶ በገዳሙ በክብር ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ተፈጽሟል ብለዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊ ለጊዜው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለገዳሙ ጥበቃ እያደረገ ሲሆን ነገሮች እስኪረጋጉ ጥበቃው እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
Source:- EOTC TV

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages