ታላቁ የአሰቦት ገዳም የእሳት አደጋ ተከስቷል - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, February 27, 2024

ታላቁ የአሰቦት ገዳም የእሳት አደጋ ተከስቷል


በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ መቆጣጠር አለመቻሉን ከሀገረ ስብከቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ትናንት የካቲት 19/2016 ዓ.ም ምሽት ተነስቷል የተባለው እሳት አሁንም እየተስፋፋ ይገኛል ብለዋል- መረጃ ሰጭያችን።
የቃጠሎ መነሻ እስካሁን እንዳልታወቀም ነግረውናል። ።
አሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ከአቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም በተደጋጋሚ ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ የሚጠቃ ሲሆን ከ3 ዓመት በፊትም በገዳሙ ደንና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ እሳት መነሳቱ ይታወሳል።
በአሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም የእሳት አደጋ የተከሰተ ሲሆን የገዳሙ አባቶች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ይገኛል። ስለሆነም የተከሰተው እሳት ከፍተኛ አደጋ ከማድረሱ በፊት ምእመናን አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ተጠይቋል። በሃገራችን ከሚገኙ ታላላቅ ገዳማት መካከል ደብረ አሰቦት አንዱ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች እንደደረሱበት ይታወቃል።
ምንጭ፤ ማህበረ ቅዱሳን


No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages