የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
++++
መልእክቱ በኦሮሚያ ክልል በዝቋላ አቦ ጥንታዊ ገዳም በወንድሞቻችን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለቅዱስነታቸው አቡነ ማትያስ በላከችው ደብዳቤ፣ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ ገዳም ላይ በደረሰው አሰቃቂ ጉዳት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን ገልጻለች። የሩሲያ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሊቀ መንበር ሜትሮፖሊታን አንቶኒ የወንጀሉን አስከፊነት በአጽንኦት ገልጸው፣ ይህም ከመለኮታዊም ሆነ ከሰው ሕግ ጋር የሚቃረን መሆኑን ተናግረዋል።
ዘገባውን ለማጠናቀር
- የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት መምሪያ ድረ ገጽ እና
- ኦርቶዶክሲ ኮግኔት ፔጅን ተጠቅመናል።
No comments:
Post a Comment