ይህን ምስኪን የጩፋ ዘመዶች ለማሳመን ብሎ ዱርየው ባለቀሚስ ሲናገር አንድ ያላስተዋለው ነገር ከአፉ አምልጦታል።
....ከእዛን ቀጠል አድርጎ ከአቡነ ጴጥሮስ የተቀበልኩት የቅስና ካርድ ስለጠፋ አዲስ አበባ ሀገረስብከት ሄጄ አቡነ ሳሙኤል ከሚባሉ ሊቀ ጳጳስ ይህን ካርድ(ቪዲዮው ላይ የሚያሳየውን ካርድ) ወስጃለው ብሎ ይተርካል።
ይህ ዱርዩ የዘነጋው አንድ ሃቅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት ክህነት ያለው አንድ አካል የክህነት ካርዱ ቢጠፋበት ቀድሞ ክህነት ወደወሰደው ሀገረስብከት በመሄድ ቀድሞ ክህነት ከመውሰዱ በፊት ያመጣቸው ፋይሎች ተጣርተው ማስረጃ ወይም ድጋሚ የክህነት መታወቂያ ካርድ ይሰጠዋል እንጅ ክህነት ካልወሰደበት ሀገረስብከት አይወስድም።
ምክንያቱም ክህነት ያልሰጠው ሀገረስብከት ስለሰውዬው የክህነት ማረጋገጫነት አንዳች ፋይል የለውም።
ቀድሞ ክህነት ያልወሰደበት ሀገረስብከት ይህ ሰው ካህን ይሁን ቦዘኔ የትኛውን ፋይሉን አጣርቶ ነው ድጋሚ የክህነት ካርድ የሚሰጠው ?
በአጭር አማረኛ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የተመረቀ መሃንዲስ ዲግሪው ስለጠፋ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ አመልክቶ የትምህርት ማስረጃውን ወሰደ እንደማለት ነው።
ቀሽም ተውኔት።
ለማንኛውም መኖክሴ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ሲመ*Fiq አዲስ አይደለም። ነገር ግን በውሸት ቄስ ነኝ መኖክሴ ነኝ ብሎ መጋጋጥ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው?
የመነfeq ሰው ምዕመን ይሁን ፓትርያሪክ በየትኛውም መመዘኛ ውሃ አያነሳም። የሁለቱም መጥፋት ስያሜው ክህደት ይባላል።
ይህ ሰው ክህነት አልባ የሆነ ሞላጫ ዱርዬ መሆኑ የምታረጋግጥበት "ከማርያም ጋር እኔን እኩል ነኝ ፣መላእክት ምንም አያውቁም፣" ማርያም እንዴት የህይወት መብልን ያገኘንባት ትባላለች?" ገለመሌ እያለ እንኳን ለኦርቶዶክስ ለቃለህይወት እና መካነኢየሱስ አማኝ እራሱ የሚሰቀጥጥ ንግግር ሲያበዛ ነበር።
እንግዲህ ጩፊዝም እንዲለመልም ውሸት ማደባሪያ ናት
Source:- ©Kune Demelash kassaye -Arba Minch
No comments:
Post a Comment