ደብረ ሲና ማርያም አንድነት ገዳም - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, September 17, 2022

ደብረ ሲና ማርያም አንድነት ገዳም

IMG_20090101_051037
ደብረ ሰላም አንድነት ገዳም በጎርጎራ ቀበሌ የምትገኝ ሲሆን የተመሰረተችው በ1312 ዓ/ም በአጼ ዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት ነው።  ይህችን ውብ ገዳም የመሰረታት የአጼ ዓምደ ጽዮን የጦር አዛዥ የሆነ ስሙ ኤስድሮስ የሚባል ነው።  ቤተ መንግስቱ ሸዋ ስለነበር በጎንደር ደንቢያ ጣና ዳር የነበሩ ቤተ አይሁዳውያን በዚያን ወቅት ለንጉሱ አንገብርም ብለው ሸፍተው ነበር። በዚህም ምክንያት የአጼ ዓምደ ጽዮን የጦር አዛዥ የሆነው ኤስድሮስ ከብዙ ሰራዊቱ ጋር ጎርጎራ ወደተባለችው ስፍራ አልገብርም ብለው ያመጹትን ሽፍቶች እንዲያስገብር ከንጉሱ ዘንድ ተላከ።  የሽፍቶችም መሪ አትርያፍ፤ ጎራድ፤ ጎርጎ፤ ስምና ይባላሉ።  የጦር አዛዡ ኤስድሮስ እነዚህን የሽፍቶች መሪ በመደምሰስ ሕዝቡ በሰላም እንዲኖርና ለሃገራችው የሚጠበቅባቸውን እንዲገብሩና ቤተ አይሁድም በሰላም እንዲኖሩ፤  ክርስትና የፍቅርና የሰላም ሃይማኖት መሆኑን እንዲማሩ በማድረግና በፍላጎታቸው ክርስትናን እንዲጠመቁ ካደረገ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያን ተከለላቸው።  የኤስድሮስ ሃገር መንዝ ደብረ ሲና ትባል ነበርና የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ደብረ ሲና ብሎ ሰየማት።  ኤስድሮስም በዚሁ አካባቢ ሳይለቅ ዳባሎ ማርያም ከምትባል ስፍራ ሕዝቡን እያስተማረ ተቀመጠ። ደብረ ሲናን በሚሰሩበት ጊዜ ግን እንደሚታወቀው የጥንት አብያተ ክርስቲያናት ሲሰሩ በ12 ሰረገላ (ወጋግራ) ነበርና ይህን ወጋግራ ለማምጣት ወደ ዘጌ (ዘንጌ) ሄዱ።   ከዘጌም የተፈለገውን ያህል አገኙ ነገር ግን ይህን ወጋግራ ለመግዛት የነበራቸው ገንዘብ ለ11ዱ ብቻ ነበር። 12ተኛው ወጋ ግራ ለመግዛት ፈልገው ገንዘብ ስላጠራቸው 11ዱን ብቻ ይዘው ወደ መጡበት ደብረ ሲና ተመለሱ።  ነገር ግን ይህን ከገዙበት ሥፍራ የቀረው ያ ወጋግራ እመቤታችን በተአምር ከሃይቁ አንከባላ በነፋስ እየተገፋ ደብረ ሲና ቀድሞ ጠብቃቸው።  እነርሱም ይህንን ገንዘብ አጥሮን ጥለነው የመጣነው ወጋግራ አይደለምን? ብለው ግራ ገባቸው ነገር ግን ይህን ያደረገች የአምላክ እናት እመቤታችን እንደሆነች ተረዱ።  ለፍጥረት አዛኝ የሆነችውን እመቤታችንን አመሰገኑዋት።  በመቀጠል እነዚህን 12ቱን ዓምዶች ከቤተ ክርስቲያኑ አቆሙት።  ይህንን ተአምረኛ ዓምድ በሴቶች ዓምድ አንቀጽ (መግቢያ) በደቡብ ምዕራብ በኩል ተከሉት። 
ግብጻዊት ማርያም ስዕል

በዚህች ገዳም ውስጥ የምትገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል ከግብጽ እንደመጣች ይነገራል።  ታሪክ እንደሚያስረዳው ከግድግዳው ያለችው ስዕለ አድኅኖ በግብጻውያን እንደተሳለች አያጠራጥርም።  ይህችን ስዕል ለየት የሚያደርጋት ነገር ቢኖር እቴጌ መለኮታዊት በልዩ ሱባኤ ከእንባ ጋር እንዳሰራቻትና ሌባ ሰርቆ ወደ ግብጽ እንደወሰዳትና በተአምር ወደ ግብጽ ተመልሳ እንደመጣች ታሪክ ያስረዳል።  ለዚህም ነው ምዕመናን ይህችን ስዕል ግብጻዊት ማርያም እያሉ የሚጠሩዋት።  መምህር አማረ የሚባሉ የብርጊዳ ገዳም አበ ምኔት ነበሩ።  ለብርጊዳ ቤተ ክርስቲያን የሚሆን ጉልላት አሰርተው ከደብረ ሲና ወደብ ሲደርሱ ታከለ ለሚባል ወጣት ውሰድ ብለው አጫጭነው ወደ ብርጊዳ ላኩት።  እርሳቸውም የደረሰ መስሎአቸው ዝም ብለው ሰነበቱ።  ከአራት ቀን በሁዋላ ቢጠይቁ ሰውየው እንዳልደረሰ ተረዱ።  ወዲያው በድንጋጤ እየጮሁ ደብረ ሲና ቤተ ክርስቲያን ገብተው ግብጻዊት ማርያም ከምትባለው ስዕል ፊት ሰግደው እመቤቴ ሆይ የላኩት ሰው ውሃ በልቶታል እያሉ ወደ እመቤታችን በለቅሶ ተማጸኑ።  ከሃዘናቸው ጽናት የተንሳ የስዕሊቱን መጋረጃ በትክሻቸው ይዘው ወደ ውጭ ወጡ።  ያን ጊዜ መምህር ተሰማ ማርያም የደብሩ አስተዳዳሪ ነበሩና የተላከው ሰው ሌባ መስሎአቸው ያዙልኝ ብለው ተደናገጡ።  በዚህም አካባቢ ከሚኖሩ ምዕመናን ጋር በመተባበር በጀልባ ፍለጋቸውን ቀጠሉ።  ከደቅ እስከ ፎገራ ጉዞአቸውን አደረጉ። ወዲያው በደቅ አካባቢ ባለው ጣና ከነታንኩዋው ይህ ወጣት ከመምህር አማረ የተቀበለውን አንድም እቃ ሳይጥል ተገኘ።  ስለ ሁኔታው ሲጠይቁት እርሱም እንዲህ ሲል አስረዳቸው።  አንዲት ቀይ ሴት በጀልባው በፊት በፊት እየመራች አይዞህ እያለችኝ ሰነበትኩ።  አሁን እናንተ ስትመጡ በዚህ ሂድ ደህና ሁን ብላኝ ሄደች አላቸው።  እነርሱም የእመቤታችን ተአምር እያደነቁ በጀልባ ጭነው ከነ ጉዋዙ አወጡት።  በተጨነቅን ጊዜ የምትደርስልንን እመቤታችን አመሰገኑዋት።

አድባራት እንዲሁም ታሪካዊ ቦታዎችን የያዘ ጥንታዊ ሐይቅ ነው ። ከእነዚህም
መካከል ፦
*ቢርጊዳ ማርያም
*ደብረ ሲና ማርያም
*መንዳባ መድኃኔ ዓለም
*ማርያም ግምብ
ጎርጎራ ግምብ
*ጎርጎራ
*ገሊላዘካሪያስ
*ናርጋ ስላሴ
*አርሲማ ሰማዕታት
*ደጋ እስጢፋኖስ
*ደቅ ደሴት
*ደጋ ደሴት
*መትራሃ
*ባርየ ግምብ (ሚካኤል)
*አብርሐ አጽብሐ ግምብ
*እንፍራዝ
*ቆጋ ልደታ
*ጋርኖ ወንዝ ድልድይ
*ጉዛራ ግምብ
*ሰንዳባ እየሱስ
*ዋሻ እንድደሴት
*ተክለ ሃይማኖት
*ታራግ ህዳም ማሪያም
*ክርስቶስ ሠምራ
*ጨቅላ ደሴት
*ጣና ቂርቆስ
*ምጽለ ፋሲለደስ
*ቆራጣ ጨርቆስ ገዳም
*ሬማ መድኃኔዓለም
*ሬማ ደሴት
*መሃል ዘጌ ጊዮርጊስ
*አቡነ በትረ ማርያም
*ይጋንዳ ተክለሃይማኖት
*ክብራን ገብርኤል
*ኡራ ኪዳነምህረት
*እንጦኖስ ደሴት
*ደብረ ማርያም
*ጣና ቂርቆስ ልሳነ ምድር
ይገኙበታል! ።
በረከትዋ ረድ ኤትዋ አማላጅነትዋ ፍቅርዋ ይደርብን አሜን።

 

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages