የታሪክ ቅሚያና ጥላቻ በኢትዮጵያ ፊደላት(የግዕዝ ቁጥሮች) ላይ - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, September 16, 2022

የታሪክ ቅሚያና ጥላቻ በኢትዮጵያ ፊደላት(የግዕዝ ቁጥሮች) ላይ

የታሪክ ቅሚያና ጥላቻ በኢትዮጵያ ፊደላትና የገዕዝ ቁጥሮች ላይ ሲነሳ እጅጉን ያሳዝነኛል፡፡ ለመሆኑ እነዚህን የገዕዝ ፊደላትና ቁጥሮችን ማን ነው የፈጠራቸው? ያልን እንደሆን፤ ብርቅየ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶቻችን ናቸው፡፡ እንኳን ፊደላትና ቁጥር ቀርቶ ሐገሪቱን የምሰረተች ይህች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ አሁን የተያዘው የፖለቲካ ቁርሾ ሃይማኖታችንን ለማጥፋት የሚደረግ መሆኑን ሃገር ያወቀው ጉዳይ ከሆነ ሰነበተ፡፡ በግልጽ እያደረጉትም ነው፡፡ እኛን ማን ይነካናል እንደፈለግን እንሆናለን እየተባለ በመከራ የተሰራችን ሃገር ለማፍረስ ጥረት አያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ እኛ ደግሞ እንኳን ፊደላችንን እና ቋንቋችንን ቀርቶ ሃገራችንን ለማዳን ስንት መስዋዕትነት እየተከፈለ እንደሆን ዓለምም ያውቃል፡፡ እኔ የማሳስበው ለሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን ይህ ፊደልና ቁጥር የሚያኮራን እንጂ የሚያሳንሰን አይደለም፡፡ ሃገራችን ምን ያህል ጥበበኛ እንደነበረች በታሪካችን ልንኮራ ይገባል፡፡ ስለዚህም በዚህ በ4ትኛ ክፍል መጽሐፍ ላይ የተጻፈውን የተንሸዋረረ ትምህርት ልንቃወምና ትክክለኛውን ልናስተምርና ልጆቻችን በሃገራቸው በታሪካቸው እንዲኮሩ ትክክለኛውን ማስተማር ይጠበቅብናል፡፡ ወላጆችም እንዲሁ መንግስት ይህን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲያስተካክል ማድረግ ወይም በፍጥነት እንዲያስተካክልና የተስተካከለ መጽሐፍ ታትሞ እንዲያቀርብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እንደኔ ሐሳብ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ይህ መስተካከል አለበት እላለሁ፡፡ ለምሳሌ ሕውሃት መንግስት በነበረበት ዘመን፤ አማራ የኦሮሞን ጡት ቆርጧል ብሎ መጽሐፍ አጽፎ ሐውልት ተክሎ ከጊዜ በኋላ እልቂት እንደፈጠረ ልንገነዘብ ይገባል፡፡ ይህ የታሪክ ጠባሳ ሆኗል፡፡ አሁን ደግሞ እየተሰራ ያለው ነገር፤ አሁን ላለው ትውልድ የኛ የግዕዝ ፊደልና ቁጥር የመጣው ከግሪክ ነው ብሎ ማስተማር ቀስ በቀስ ታሪክን ማጥፋት ስለሆነ እኛው አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል ብለን ሕዝባችንን የግዕዝ ቋንቋውንና ፊደሉን ቁጥሩን ልናስተምረው ይገባል እላለሁ፡፡ በአዲሱ የትምህርት ዘመን በተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ ላይ የተገኘ "መርዝ ቁጥር -፩ መምህራን ይሄንን ለልጆች ቢያስተምሩ ወላጆች ትክክለኛውን እውቀት በማስረጃ ያስረዷቸው ዘንድ ሀላፊነት አለባቸው። ወላጆች ልጆቻቸው የሚማሩባቸውን መጽሐፍት ማየትና መገምገም ያስፈልጋል። መምህራንም በሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ላይ ሀላፊነት አለባቸውና እውነቱን በመናገር ፣ሀሰቱን በማጋለጥ ተማሪዎቻቸውን እንዲያስተምሩ ይገባል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተጻፈ ስህተት፣ጥላቻ እና በመጽሐፍቶቹ እንክርዳድ ተዘርቶባቸው ከሆነም መምህሩ እውነታውን በማጋለጥ የትውልድ ሀላፊነቱን ይወጣ። የታሪክ ቅሚያና ጥላቻ ካለበት ያስተውል፣ እውነትን ይናገር። የኢትዮጵያ ፊደላት(የግዕዝ ቁጥሮች) በኢትዮጵያውያን አባቶቻችን የተፈጠሩ ናቸው። ኮርተን የምንናገረው፣ የምናስተምረው ሐቅ‼ የታሪክ ቅሚያና ጥላቻ የኢትዮጵያ ፊደላት(የግዕዝ ቁጥሮች) በኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶቻችን የተፈጠሩ ናቸው።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages