ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጠቅላይ ቤተክህነት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ። - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, November 5, 2022

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጠቅላይ ቤተክህነት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ።

 




ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም

አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊያን አባቶች ሰርተው ያቆዩላትን ቤቶችና ሕንጻዎች በመጠቀም የምታገኘውን ገቢ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተግባራቷን ለማከናወን የምትጠቀምበት ሲሆን ያሉትን መጠቀሙ እንደተጠበቀ ሆኖ ዘመኑን የዋጁ ተጨማሪ የልማት ሥራዎችን በማከናወን የቤተክርስቲያናችንን ገቢ ማሳደግ እንደሚገባ ጽኑዕ አእምነት ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሰጣቸው ተደጋጋሚ ትዕዛዞችና ባስተላለፋቸው ውሳኔዎች አማካኝነት በአራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት፣በአሮጌው ቄራና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ቅጽረ ጊቢ ውስጥ ሁለገብ ሕንጻዎችና ዘመናዊ የስብከተወንጌል አዳራሽ እየተገነቡ ይገኛሉ።
ይህ የልማት ሥራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃት ይችል ዘንድ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ኃላፊነት በመጡ ማግስት የግንባታ ሥራዎቹ ያሉበትን ሁኔታ መሰረት ያደረገ የጉብኝት መርሐ ግብር በማካሔድና አጠቃላይ የሥራውን ሁኔታ በአስተዳደር ጉባኤ በመገምገም በአሰሰቸኳይ የልማት ሥራው የሚቀላጠፍበትን ሁኔታ መሰረት ያደረገ አቅጣጫ በመስጠትና የግንባታ ሥራውን አፈጻጸም በሪፖርትና በአካላዊ የመስክ ጉብኝት በመከታተል የግንባታዎቹ የሥራ አፈጻጸም ውጤታማና ቀልጣፋ መሆን እንዲችል አድርገዋል።
ይህን ተከትሎም በተለይ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትና በባሻ ወልዴ ችሎት በመገንባት ላይ የሚገኙት የግንባታ ሥራዎች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተጎብኝተዋል።በዚሁ የጉብኝት መርሐ ግብር ላይ በሕንጻዎቹ የግንባታ አፈጻጸም ዙሪያ በባለሙያዎች ገለጻ የተደረገ ሲሆን በተለይም የሁለቱ ሕንጻዎች አፈጻጸም ባለፉት ስድስት ወራት ከፍተኛ መሻሻልን ያሳየ መሆኑ ተገልጿል።የሕንጻ ግንባታውን ሂደቴና ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ የተመለከቱ ብፁአን አባቶችም በተመለከቱት የልማት ሥራ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከእርሳቸው በፊት የተጀመሩ አራት ሁለ ገብ ሕንጻዎችን ከማስጨረስ ባለፈ የምግባረ ሰናይ ዘመናዊ ሆስፒታል ግንባታን የማስገንባት ኃላፊነት ያለባቸው ቢሆንም በረቀቀ የአመራር ጥበባቸውና ባካበቱት ልማትን ውጤታማ የማድረግ ልዩ ከህሎት ከፍጻሜ እንደሚያደርሱት ጥርጥር የለውም ።ስለሆነም በየደረጃው የሚገኙ የቤተክርስቲያን አመራር አካላት አስፈላጊውን ሁሉ በመፈጸም በተግባር የብፁዕነታቸውን የማያወላዳ ውሳኔ በመፈጸምና በማስፈጸም የተጀመሩና አዲስ የሚሰሩ የልማት ሥራዎች ፍጻሜ እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
 
Source:  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages