ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት 26 - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, March 4, 2023

ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት 26

 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

የካቲት ሀያ ስድስት በዚህች እለት #ነቢይ_ሆሴዕ አረፈ፣ የከበረ #ቅዱስ_ሳዶቅ በሰማእትነት አረፈ።


የካቲት ሀያ ስድስት በዚህች እለት ዖዝያ ይባል የነበረ እውነተኛ ነቢይ ሆሴዕ አረፈ። ዳግመኛም ይህ ነቢይ በአራቱ የይሁዳ ነገሥታት ዘመን ትንቢት ተናገረ። እሊህመ ዖዝያን ኢዮአታም አካዝ ህዝቅያስ ናቸው። በትንቢቱም ድንቆች ስራዎችን ተናገረ የእስራኤልንም ልጆች ብሎም ጠራቸው እግዚአብሔርም ቁጣውን ከእርሳቸው እንደማይመልስ አስረዳቸው።
እንዲህም አለ የእስራኤል ልጆች ቁጥራቸው እንደማይሰፈርና እንደማይቁጠር የባህር አሸዋ ቢሆን ከጥቂት በቀር አይተርፍም አለ። ስለ አህዛብም በእግዚአብሔር ማመን ተናገረ እንዲህም አለ እኔ ወገኖቼ ያልሆኑትን እጠራቸዋለሁ እነርሱም ይሰሙኞል።
ዳግመኛም ስለ መድኃኒታችን መከራ መቀበልና በከበረ ደሙ ስለ መዳናችን ስለ ትንሳኤውም እንዲህ ብሎ ተናገረ።እሱ በመከራ ገርፎ ይድነናል እርሱም በመከራ አቁስሎ ይቅር ይለናል ሲያድነንም በሁለተኛው ቀን ነው ።
በሶስትኛውም ቀን ድነን በሱ ፊት እንነሳለን እግዚአብሔርንም አውቀን እንከተለው ዘንድ ስለ ሞት ስልጣን መሻር ስለ መቃብርም መሸነፍ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ ሞት ይዘህ ማስቀረትህ መቃብርስ ድል መንሳትህ ወዴት ነው ትንቢትን እየተናገረ ሰባ ዓመት ያህል ኑሮ በበጎ ሽምግልና አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
በዚህችም እለት የከበሩ ሳዶቅና ከእርሱ ጋር የሆኑ ሁለት ሺህ ስምንት ሰዎች በሰማእትነት አረፉ። ይህንንም የከበረ ሳዶቅን ለፀሐይ ይሰግድ ዘንድ የፋርስ ንጉሥ ብርህም ፈለገው ቅዱሱም ለፈጣሪዋ እንጂ ለዚች ለምትታይ ፀሐይ ልሰግድ ከእናቴ ማህፀን አልወጣሁም ብሎ መለሰለት።
ብርህም ንጉሡም መልሶ ለዚች ፀሀይ አምላክ አላትን አለው ቅዱስ ሳዶቅም አለሙን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ አምላክ ነው አለው ።ንጉሡም የቅዱስ ሳዶቅን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የከበረ ሳዶቅም ቁሞ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ከዚህም በኋላ ራሱን ዘንበል አድርጎ ቆረጡት።
ያን ጊዜ ከሰማይ ብርሃን በላዩ ወረደ ከዚያ ያሉትም ሁሉ አይተው እኛ ሁላችንም በቅዱስ ሳዶቅ አምላክ የምናምን ክርስቲያን ነን ብለው ጮኹ ንጉሱም ሁሉንም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግስተ ሰማያት ተቀበሉ ቊጥራቸውም ሁለት ሺህ ስምንት ነፍስ ናቸው።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትሁን አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages