ቀዳሚት ሥዑር - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 14, 2023

ቀዳሚት ሥዑር


ዐባይ ሰንበት፣ ቀዳሚት ሥዑር ትባላለች። ዐባይ ሰንበት መባሏ ጌታ በጥንተ ፍጥረት ከእሁድ እስከ አርብ ስድስቱን ቀናት ሲፈጥር ሰንብቶ በሰባተኛዋ በቀዳሚት አልፈጠረም። ዕረፉባት ሲል ሥራውን ፈጽሞ አርፎባታል። “ወአእረፈ እግዚእነ እምኩሉ ዘአኀዘ ይግበር” እንዲል ዘጸ ፳፥፲፩

5500 ዘመን ሲፈጸምም ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ተወልዶ ሰው ሰውኛውን ኖሮ የማዳኑን ሥራ ዐርብ በመልዕልተ መስቀል ፈጽሞ በአዲስ መቃብር አርፎ ውሎባታልና ስለዚህ ነው።
ስዑር መባሏም ደቀመዛሙርቱ ዓርብ ሕማሙን ሞቱን አይተው እሞታለሁ ብሎን ሕማሙን ሞቱን አየን፤ እነሳለሁ እንዳለንስ ትንሣኤውን ሳናይ እንቀራለን ብለው ከምግብ ተከልክለው ሲያዝኑ ውለዋል። ስዑር መባሏ ብትሻር አይደለምን ብለው ሲሰሩባት ተድላ ደስታ ሲያደርጉባት የሚውሉ ቢኖሩም እውነታው ግን እንዳልነው ሕማሙን ሞቱን እያሰብን የምንጾምባት የምናዝንበት ስለሆነ ነው።
በነግህ ካህናት የነግህ ተግባራቸውን አድርሰው “ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሀደ ለኩሉ” እያሉ በዘመነ ኖህ ርግብ “ሐጸ ማየ አይኅ፤ ነትገ ማየ ድምሳሴ” ስትል ቄጠማ የወይራ ቅጠል ይዛ እንደተገኘች “ሐጸ ማየ ኃጢአት፤ ነትገ ማየ መርገም” ሲሉ ቄጤማ ለምእመናን ያድላሉ።
እግዚአብሔር በሰላም፤
ያለደዌና ያለ ሕማም፤
ያለጻዕርና ያለ ድካም፤
ለብርሃነ ትንሣኤው ያድርሰን ያድርሳችሁ።
ምንጭ፡ መዝገበ ታሪክ 2 ገጽ 35

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages