ሥርዓተ ጸሎት ወስግደት ዘዓርብ ስቅለት - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, April 14, 2023

ሥርዓተ ጸሎት ወስግደት ዘዓርብ ስቅለት



ዐርብ ጠዋት በ፲፪ ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም ርግዘተ ገቦሁ ነአምን ወቅንዋተ እደዊሁ ነአምን ዬ ዬ ዬ ነአምን ሞቶ ወትንሣኤሁ
በመቀጠል "ለከ ሃይል" ይባላል ከኦሪት ምንባብ እስከ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል
ምስባክ መዝ ፳፮ ፥ ፲፪
እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ
ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ
እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ
ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በዜማ በኅብረት ይበሉ
ማቴ 27፥1-14 ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ይስቅልዎ ለኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል
ማር 15፥1-5 ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ
ሉቃ 22፥66-71ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወመጠውዎ ለጲላጦስ
ዮሐ 19፥29- 40ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወነበረ ዐውደ ሶቤሃ
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን "መልክዐ ሕማማት" ያድርሱ
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "እብኖዲ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ታኦስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ማስያስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ኢየሱስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ክርስቶስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "አማኑኤል" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ትስቡጣ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ........... ፵፩ ጊዜ

ጠዋት በ፫ ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) አርዑተ መስቀል ፆረ (፪) ይስቅልዎ ሖረ ዬ ዬ ዬ ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚእ ኮነ ገብረ
በመቀጠል "ለከ ሃይል" ይባላል ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል
ዲያቆኑ መዝሙር ፴፬ትን ፫ ቦታ ከፍሎ በውርድ ንባብ ይበል በቀመጠል ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል እየተሰገደ
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ
ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ
ምስባክ መዝ ፳፩ ፥፲፮
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን
ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን
ማቴ27፥15-17 ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አኃዝዎ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ
ማር 15፥6-15 ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሀበ ሎሙ ኢየሱስሃ ይስቅሉ
ሉቃ 23፥13-25 ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኲናን
ዮሐ 19፥1-12 ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ" ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን መልክዓ ሕማማት ያድርሱ
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "እብኖዲ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ታኦስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ማስያስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ኢየሱስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ክርስቶስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "አማኑኤል" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ትስቡጣ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ........... ፵፩ ጊዜ

አርብ በስድስት ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ተሰቅለ (፫) ወሐመ ቤዛ ኲሉ ኮነ ዬ ዬ ዬ በመስቀሉ ቤዘወነ እሞት ባልሐነ
በመቀጠል "ለከ ሃይል" ይባላል ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል
ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከገላትያ በውርድ ንባብ ይበል ከዚያም ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ
ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ
ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኲልነ
ይእዜኒ ወዘልፈኒ
ምስባክ መዝ ፳፩ ፥ ፲፮
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ
ወኆለቊ ኲሎ አዕፅምትየ
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ
ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ
ማቴ 27፥27-40 ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ
ማር 15፥17-43ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ዐበጥዎ ለስምኦን ከመ ይፁር መስቀሉ
ሉቃ23 -27- 44ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን
ዮሐ 19፥13-27 ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ቀትር ሶቤሃ ሊቃነ ካህናት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ፪ኤ ፈያት
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ" ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን መልክአ ሕማማት ያድርሱ።
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "እብኖዲ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ታኦስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ማስያስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ኢየሱስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ክርስቶስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "አማኑኤል" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ትስቡጣ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ........... ፵፩ ጊዜ

ዐርብ በዘጠኝ ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ሶበ ሰቀልዎ(፫) ለእግዚእነ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ዬ ዬ ዬ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት
በመቀጠል " ለከ ሃይል" ይባላል ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ምንባብ ይነበባል ከዚያም በኃላ ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ
ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከ ግብረ ሕማማት በውርድ ንባብ ይበል በመቀጠልም ሶስት ካህናትና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በስዕለ ስቅለት ፊት ይቀመጡ ከአንዲት መብራት በቀር ሌላውን ያጥፉና አንድ ግምጃ በራሳቸውና ገፃቸው ላይ ያድርጉ (ምዕመናን ደግሞ በነጠላቸው ይሸፈኑ) አንገታቸውን ዝቅ አድርገው በዕዝል ዜማ በታላቅ ድምጽ በሀዘንና በፍርሃት በለቅሶና በዕንባ ጭምር ካህኑና ሕዝቡ በመቀባበል "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን ሦስት ሦስት ጊዜ ይዝለቁ እንደገናም "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን አንድ አንድ ጊዜ በመቀባበል በሁለት ዙር (አጠቃላይ ቁጥሩ ፲፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ ዲያቆኑም በየክፍሉ በውርድ ንባብ እያስገባ ያንብብ
አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ
ይ.ሕ በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ
ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፷፰ : ፳፮
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ
ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ
ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ
ማቴ 27 ፥ 46-50 ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ
ማር15፣40-47 ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ
ሉቃ 23፥45 47 ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ
ዮሐ 19፥29 - 30ከተነበበ በኋላ
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን_መልክዐ_ሕማማት ያድርሱ።
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "እብኖዲ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ታኦስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ማስያስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ኢየሱስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ክርስቶስ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "አማኑኤል" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን "ትስቡጣ" ናይናን ኪሪያላይሶን
ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ኪሪያላይሶን ........... ፵፩ ጊዜ

በአስራ አንድ ሰዓት
አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሃተ ዘእንበለ ዐቅም ዬ ዬ ዬ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ፤ እንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ
በዚህ ሰዓት "ለከ ሃይል" ኪርያላይሶንና መልክዐ ሕማማት" የለም
ሥርዓተ እግዚኦታ
ካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ሥርዓተ ግንዘትን ይስሩ ሦስት ካህናትም ሥርዓተ ግንዘቱን በእጃቸው አቅፈው ይያዙት አንድ ካህን መስቀልና ጽንሐሕ ይዞ በኋላቸው ይከተል አንድ ዲያቆን ደግሞ መስቀልና መብራት በመያዝ ፊት ለፊት ይምራ በምዕራብ በኩል ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ይቁሙ ከዚህ በኋላ በአራቱም ማዕዘናት እየዞሩ እግዚኦታ ያድርሱ አደራረሱም ካህናቱና ሕዝቡ በግራና በቀኝ በአራቱም አቅጣጫ በአራት ተመድበው በመቆም በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ በንዑስ ዜማ ባለአምስቱን ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ እንደገና በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ በንዑስ ዜማ በእንተ ማርያም ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ ነው
ምሕላው ከተፈጸመ በኋላ ካህኑ አቡነ ዘበሰማያት ይስጥ እስከ ትንሣኤ ድረስ የኑዛዜ ጸሎት ስለሌለ ካህኑ ፵፩ ጊዜ ኪርያላይሶን ይበል ሕዝቡም እንደርሱ ይበሉ
ከዚህ በኋላ በቅኔ ማኅሌት ሁሉም ይሰብሰቡ መቋሚያ ይዘው በመካከላቸው ጧፍ አብርተው ይያዙ የዳዊትንና የነቢያትንም ጸሎት እየተቀባበሉ ያንብቡ አንብበው ሲጨርሱ በመካከላቸው ያለውን መብራት በያዙት መቋሚያ ያጥፉት የዲያቢሎስ ገዢነት መደምሰስ ምሳሌ ነው።
ከዚያም መዘምራን ንሴብሖን ይዘምሩ ካህናትም ሕዝቡን በወይራ ቅጠል እየጠበጠቡ እና ስግደት እየሰጡ ወደ ቤታቸው ይሸኟቸው።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages