ቀኖና ዘኒቅያ (ዘሠለስቱ ምእት)
ቀኖና ፩:- በሕመም ምክንያት የተሰለበ ወይም ሌሎች በግድ የሰለቡት ሰው በቅቶ ከተገኘ ክህነት ከመሾም አይከልከል። ሳይታመም ወይም ሳያስገድዱት በፈቃዱ ራሱን የሰለበ ሰው ግን ምእመን ቢሆን ክህነት አይሾም። ካህን ቢሆን ከክህነቱ ይሻር።
ቀኖና ፪:- አዲስ አማኝን በደንብ ሳይፈትኑት ወደ ክህነት አያምጡት።
ቀኖና ፭:- ከባድ ምክንያት ሳያጋጥመው ቤተክርስቲያን አልገባም የሚል ካህን ሕዝባዊ ካለ ይገሥጹት። በኤጲስ ቆጶሱ ላይ ክፉ የሚያደርግ ሰው ካለ ይገሥጹት። ኤጲስ ቆጶሱም በቂምና በቁጣ በአንዱ ላይ ክፉ ቢያደርግ ይሻሩት። ኤጲስ ቆጶሳት ወደ ጳጳሳቸው በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰብሰቡ።
ቀኖና ፮:- ኤጲስ ቆጶስ ያለሕዝቡና ያለጳጳሱ ፈቃድ አይሾም። ከግማሽ በላይ ሕዝብ ከተቃወመው ኤጲስ ቆጶስነትን አይሾም።
ቀኖና ፰:- ወደ ትክክለኛዋ ሃይማኖት ካልተመለሱ የከሓድያንን ንስሓቸውን አይቀበሏቸው።
ቀኖና ፱:- ሳይመረምሩ የሾሙት ቄስ ቢኖር ከተሾመ በኋላ ቀድሞ የሠራው በደል ቢታወቅ ሹመቱ ተቀባይነት የለውም።
ቀኖና ፲፩:- ማንም ሳያስገድደው በፈቃዱ የካደ ሰው ቢኖርና በኋላ ንስሓ ቢገባ ይቀበሉት። ያልተገባው ሆኖ ቢገኝ ግን አይቀበሉት።
ቀኖና ፲፪:- ዓለምን ከናቃት በኋላ ወደዓለም የሚመለስ ሰው ቢኖር ቀኖናው 10 ዓመት ይሁን። በተጨማሪም 3 ዓመት ከንኡሰ ክርስቲያን ጋር ይማር።
ቀኖና ፲፫:- ለሞት የደረሰ በንስሓ ከምእመናን የተለየ ሰው ቢኖር ሊቆርብ ቢፈልግ ያቁርቡት። ከቆረበ በኋላ ከዳነም ከምእመናን ጋር ይቀላቀል።
ቀኖና ፲፬:- ክዶ የተመለሰ ሰው ቢኖር ሦስት ዓመት ከንኡሰ ክርስቲያን ጋር ቆይቶ ወደ ምእመናን ይመለስ።
ቀኖና ፲፭:- ቀሳውስት ዲያቆናት የተሾሙባትን ቤተክርስቲያን ትተው ወደ ሌላ ቤተክርስቲያን አይሂዱ። ይህን ያደረጉ ካሉ ሲኖዶስ ያወግዛቸዋል።
ቀኖና ፲፮:- ከሌላ ቤተክርስቲያን የመጣን ቄስ ወይም ዲያቆን አይቀበሉት። ወደ ቤተክርስቲያኑ ይመልሱት እንጂ።
ቀኖና ፲፯:- አራጣ የሚቀበል ካህን ቢኖር ከሹመቱ ይሻር።
ቀኖና ፲፰:- ካህናት ሹመታቸው እንደ ሠራዊተ ብርሃን እንደሆነ ሊረዱ ይገባል። ዲያቆናት ቁርባንን ከቄስ ወይም ከኤጲስ ቆጶስ ይቀበሉ እንጂ በእጃቸው አይቀበሉ። ይህን ሥርዓት ያፈረሰ ቢኖር ከክህነቱ ይሻር።
ቀኖና ፲፱:- ከከሓድያን ወደእኛ የተመለሰ ሰው ቢኖር ዳግመኛ ያጥምቁት። የከሓድያን ጥምቀት ከጥምቀት አይቆጠርምና። ከተጠመቀ በኋላ ምግባሩ ያማረ ሆኖ ቢገኝ ክህነት ይሾም። ዲያቆናውያትና መነኮሳይያት ለአገልግሎት ቢለዩም ቁጥራቸው ከሕዝባውያት ነው።
ቀኖና ፳:- በሰንበታትና በበዓለ ኃምሳ አይስገዱ።
ይህንን ቀኖና ሠለስቱ ምእት አርዮስን ካወገዙ በኋላ የሠሩት ነው።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
No comments:
Post a Comment