የመጪዉ ዐሥርት ዓመታት የመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት ግቦች ዙርያ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው።
ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በመሪ ዕቅድ መምሪያ አሰናጅነት "ኑ የእግዚአብሔርን ቤት በጋራ እንሥራ" በሚል ርዕስ የመጪዉ ዐሥርት ዓመታት በመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት ግቦች ዙርያ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው።
በመድረኩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የመጪዉ ዐሥርት ዓመታት የመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት / ከ 2016 ዓ.ም - 2025ዓ.ም/ Orthodox Spiritual and Sustainable Development Goals (OS-SDG) ዙሪያ በባለሙያዎች ማብራሪያ ቀርቧል።
ምንጭ፤ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
No comments:
Post a Comment