#ደብረ_ዘመዳ_ጀመዶ_ማርያም_የዋሻ_ውስጥ_ገዳም_ወሎ_ራያ_ቆቦ! - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, May 18, 2020

#ደብረ_ዘመዳ_ጀመዶ_ማርያም_የዋሻ_ውስጥ_ገዳም_ወሎ_ራያ_ቆቦ!

/እንኳን አደረሰን/
ጀመዶ ወይም ዘመዳ ማርያም በመባል የምትታወቀው ከ1000 ሽ አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረች ገዳም ስትሆን በወሎ/ቤተ አማራ/በሰሜን ወሎ ከወልዲያ 70 ኪሎሜትር ርቃ የምትገኝ ሲሆን ርዝመቱ 15 ሜትር ወርዱ ደግሞ 7 ሜትር ከፍታው (ቁመቱ) ደግሞ በአማካይ 20 ሜትር የሚሆን ዋሻ ውስጥ በልዩ የግንባታ ጥበብ ታንፃና በቅዱሳን ስእል አሸብርቃ የምትገኝ ገዳም ናት። ይቺ የዋሻ ገዳም ከወልዲያ 70 ኪሜ ርቀት ላይ ከምትገኘው የዋጃ ከተማ ተገንጥሎ በሚወስደው አስቸጋሪ የእግር መንገድ በሚጠይቀው የግዳን ወረዳ ውስጥ ሲሆን ያለችው፣ እንደ ሃይማኖት አባቶች አባባል ከተመሰረትች 1000 አመታትን አስቆጥራለች።
የጀመዶ ገዳምን ካሸበረቋት ስእሎች መካከል የገዳሟ ልዩ የክብር ምንጭ የሆነው በወንጌላዊው ሉቃስ እንደተሳለች የሚነገርላት "#ምስለ_ፍቁር_ወልዳ" በሚል መጠሪያ የምትታወቀው የቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ነው። ጥቅምት 4 እና ግንቦት 1 ቀን በሚውሉት የገዳሟ አመታዊ ክብረ በአሎች የ"ምስለፍቁር ወልዳ" ስዕል በመጋረጃ ተሸፍና፣ በሶስት ቀሳውስት በጥንቃቄ ተይዛና በዝማሬ ታጅባ ትወጣለች። ለመቆሚያ በተዘጋጀው የስጋጃ ምንጣፍ ላይም ሲደርስ መሸፈኛው ተገልጦ ስእሏ ለምእመናን እንድትታይ ይደረጋል። ምእመናኑም "ለምስለ ፍቁር ወልዳ" ያላቸው ሃይማኖታዊ ክብር እጅግ በደመቀ እልልታ እና በስግደት የገልፃሉ።
ሀገራችን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ከክፉ ነገር ትጠብቅልን።
Image may contain: crowd and outdoor

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages