መርጦ_ለማርያም_ዘጎጃም - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Monday, May 18, 2020

መርጦ_ለማርያም_ዘጎጃም


  • በኢትዮጵያ ቀደምት መስኦተ ኦሪት ከሚፈፀምባቸው ከአራቱ አንደኛዋ

  • ከ2000ዓ.ዓ ጀምሮ የነገደ ካም የኩሽ ዘሮች የጊዮንን ወንዝ ተከትለው የመጡትን የተቀበለች፡፡

  • በጎጃም ክፍለ ሃገር የመጀመሪዋ ከተማ መርጦ ለማርያም

  • በዚች ስፍራ ህገ ልቦና በኋላም ህገ ኦሪት ተመልኮባታል፡፡

  • ጥንታዊ የሆኑ የቅርስ ባለቤት

ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም ገዳም በጎጃም ክፍለ ሃገር ከሚገኙ ቅዱሳት አያሌ ገዳማት መካከል አንዱአ የታላቋ እና የጥንታዊቷ ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያምጋዳም የምትገኘው ናት ።

ይህች ጥንታዊ ገዳም የምትገኘው ከአዲስ አበባ ሰሜናዊ አቅጣጫ 364 ኪሎ ሜትር ርቀት በአሁኑ በምስራቅ ጎጃም ዞን ትገኛለች፡፡ ከተማዋ በጎጃም ክፍለ ሃገር የመጀመሪዋ እንደሆነችም ይነገርላታል፡፡

በጎጃም ክፍለ ሃገር በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ርዕሰ ከተማ መርጡለ ማርያም ከአ.አ በሰሜን አቅጣጫ ትገኛለችመርጡለ ማርያም ትርጉሙ ~የማርያም አዳራሽ ማለት ነው ።

ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም አሁን የያዘችውን የስም መጠሪያ ከመያዝዋ በፊት በተለያዩ ዘመናት 4ግዜ የስም መለዋወጦች አጋጥሟታል። መጀመሪያ ሃገረ ሰላም ተብላለች ቀጥሎሃገረ እግዚአብሔር ተብላለች ቀጥሎ ጽርሐ አርያም ተብላ ተጠርታለች በመጨረሻም አሁን የምትጠራበትን መርጡለ ማርያም የሚለውን ስያሜ አግኝታለች ። የገዳሟ አስተዳዳሪ ርእሰ ርኡሳን የሚል ስያሜ አለው።

ይህችታላቅ እና ጥንታዊ ገዳም የተመሰረተችው ከእስራኤሉ ንጉስ ሰላሞን ከኢትዮጵያዊቷ ንግስት ሳባ (ማክዳ) የተወለደው ቀዳማዊ ሚኒሊክ ይዟቸው በመጣ ፫፻፲፰ የኦሪት ካህናት በአራት ሺ አምስት መቶ አመተ አለም ነው።

ወደዚች ቦታ የመጡ የኦሪት ካህናት መስዋተ ኦሪትን በመስዋተ የኦሪት አምላኮት ሲፈፅሙ ኖረዋል ። ፫፻፴፫ዓ.ም ህሩያን መገስታት አብርሃ ወ አፅብሃ ከከሳቴ ብርሃን አባ ሰላም ጋ በመሆን ከዚህች ቦታ መተው ህገወንጌል አስተምረዋል ህዝቡን አጥምቀው ካህናት ሹመዋል።
No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages