ቀዳሜ አድባራት አበራ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ጎንደር - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, June 2, 2020

ቀዳሜ አድባራት አበራ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ጎንደር


🌱ሰንበት ት/ቤት ዘጎንደር🌱
እናስተዋውቃችሁ- ፭
🍂የሰ/ት/ቤቱ ሥም :- ቀዳሜ አድባራት አበራ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት
🍂ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ጊዜ :- በ 1406 ዓ.ም በአፄ ይስሃቅ ዘመነ መንግስት ሲሆን ከጎንደር አርባ አራቱ ታቦታት አንዱ ነው፡፡
🍂ዓመታዊ ክብረ በዓል፦ ሚያዚያ 23፣ጥር 17፣ህዳር 12 እና ሰኔ 12
🍂ሰ/ት/ቤቱ የምሥረታ ጊዜ:- 1994 ዓ.ም
🍂መገኛ ሀገረ ስብከት:-በማ/ጎንደር ሀገረ ስብከት በጎንደር ርዕሰ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት
🍂የቤተ ክርስቲያኑ አድራሻ፤ ጎንደር ማራኪ ክ/ከተማ ቀበሌ 18
🍂የሰ/ት/ቤቱ የጉባዔ አከፋፈል፤ የህጻናት፣ማዕከላውያን እና የአዋቂዎች
፩/የህፃናት ጉባኤ መርሐ ግብሮች-
➡️ለ/መደበኛ ጉባዔ መርሐ ግብር ቅዳሜ ከ4 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት እና እሁድ
፪/ ማዕከላውያን መርሐ ግብር
➡️ሀ/ ሀሙስ እና ቅዳሜ ከ11:30-12:30 የተከታታይ ትምህርት
➡️ለ/ማክሰኞ ከ 11:30-12:30 መዝሙር ጥናት
➡️ሐ/ረቡዕ 11:30-12:30 ጸሎት መርሐ ግብር
➡️መ/መደበኛ መርሐ ግብር፡ እሁድ ከ7:00-9:00 መርሐ ግብር
3/ የአዋቂዎች ጉባኤ መርሐ ግብሮች
➡️ሀ/የጸሎት መርሐ ግብር አርብ ከ11:30-12:30
➡️ለ/የመዝሙር ጥናት መርሐ ግብር: ረቡዕ ከ11:30-12:30
➡️ሐ/ የቤተሰብ ውይይት መርሐ ግብር: ሀሙሰ ከ11:30-12:30
➡️መ/ተከታታይ ትምህርት ሰኞ እና ማክሰኞ ከ11:30-12:30
➡️ሠ/ልሳነ ግዕዝ እና የሥርአተ ቅዳሴ ትምህርት ቅዳሜ ከ10:00-12:30
➡️ረ/ የመደበኛ መርሐ ግብር እሁድ ከ9:00-11:00
🍂በደብሩ የሚገኙ የአብነት ት/ቤቶች
➡️፩/የቅኔ ትምህርት ቤት
➡️፬/አቋቋም ትምህርት ቤት
🍂የደብሩ አዋሳኞች
➡️በምስራቅ:- ፊት አቦ ቤተ ክርስቲያን
➡️በምዕራብ:- ቀራኒዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
➡️በሰሜን:- ደብረ ሃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን
➡️በደቡብ:-ምስራቀ ፀሀይ አቡነ ሐራ ድንግል ቤተ ክርስቲያን
🍂ከሰ/ት/ቤቱ አርያአነት ያለው ተሞክሮ ፤
፩/ከቤተ ክርስቲያኑ ሰበካ ጉባዔ ጋር ጥሩ ግንኙነት መኖሩ እና ተናቦ መስራቱ
፪/በሰ/ት/ቤቱ ያደጉ ለሰ/ት/ቤቱ መደበኛ መርሐ ግብር፣ተከታታይ ትምህርት እና በተለያዩ ቦታዎች እየተጋበዙ አገልግሎት የሚሰጡ መምህራን ማፍራቱ
፫/ከሰኞ እስከ እሁድ ቋሚ የሆነ የሰርክ መርሐ ግብርን መምራትና ማስተባር መቻሉ
፬/በመንፈሳዊ ህይወታቸው አርአያነት ያለቸውና በሥጋዊ እውቀታቸው ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ በተለያዩ ትልልቅ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችና የትምህርት ተቋማት የሚመሩ አባላትን ማፍራቱ፡፡
፭/የራሱን ስርዓተ ትምህርት በመቅረጽ ተከታታይ ትምህርቶችን አጠናክሮ እየሰጠ መሆኑተ
፮/ንዋየ ቅድሳት ሱቅ መሸጫ ያለው መሆኑ
➡️የሰ/ት/ቤቱ ሰብሳቢ፡ ዲ/ን ሰሎሞን ሲሳይ 09 00 43 76 30

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages