ታናሽ በተባልክበት ክፉ ወራት አንድ ቀን የሚከናወነውን የታላቅነትህን ምሥጢር በእግዚአብሔር የተስፋ መዝገብ በኩል ባለው ራዕይ እያገላበጥክ አንብብ። ያን ግዜ ወጀቡ ቢበዛም ተስፋ አትቆርጥም''
“መልካም ሰዎችን በውጫዊ ውበታቸው ወይም በመልካቸው አትለያቸውም። ነገር ግን በግብራቸው በመንፈሳቸው በተገኙበት አከባቢ በሚፈጥሩት ጥሩ ድባብ ነው። ምክንያቱም ማንም ከመንፈሱ ያልሆነ አከባቢ መፍጠር አይችልም ” ብዙ ሰዎች የመንፈሳቸው ያልሆነውን አካባቢ ለመፍጠር ሲሞክሩ ይታያል ነገር ግን የማይሆን ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመገዛት የመንፈስ ፍሬዎችን ያፈራል አካባቢውንም በፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ይመላዋል። (ገላ ፭፥፳፪)። አካባቢያችን እንዲለወጥ ለመንፈስ ቅዱስ እንገዛ ያኔ መልካምነታችን ለሌሎች ይታያል።
የማልረባ ታናሽ ባርያ ነኝ ብለህ ራስህን ዝቅ ማድረግህ ጥሩ ቢሆንም ተስፋ እንዳትቆርጥ ግን እንደ ሙሴ የተስፋይቱን ምድር አሻግረህ ተመልከት። ሊቀ ነቢያት ሙሴ አንደበተ ኮልታፋ ቢሆንም ባለራዕይ ነው። እግዚአብሔርን መሻትና ባልንጀራን መውደድም በውስጡ ነበረ፣ በትህትናውና በየዋህነቱ ከነቢያት ሁሉ በላይ ከእግዚአብሔር ጋር ለ፭፻፸ ጊዜ ያህል ተነጋግሯል።
ከፍ፡ከፍ፡ስትል፡ስንፍናን፡ያደረግህ ፡እንደ፡ኾነ፥ክፉም፡ያሰብህ፡እንደ፡ኾነ፥እጅህን፡በአፍህ፡ላይ፡ ጫን።ወተት፡መግፋት፡ቅቤን፡ያወጣል፥አፍንጫንም፡መጭመቅ፡ደምን፡ያወጣ፤እንዲሁም፡ቍጣን፡መጐተት፡ጠብን፡ያወጣል። ምሳ፴÷፴፫
No comments:
Post a Comment