የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ ጉባኤ ውሎው ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, October 27, 2022

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ ጉባኤ ውሎው ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም

 

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ ጉባኤ ውሎው
ተሻሽሎ የቀረበውን ህገ ቤተክርስቲያን አጸደቀ፤ሌሎች
ሁለት አጀንዳዎች ላይም ሰፊ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አስተላልፏል።
 

 

ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም

አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው እለት ባካሔደው ጉባኤ በሦስት አጀንዳዎች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አስተላልፏል።
ምልአተ ጉባኤው በትላንትናው እለት ባካሔደው ጉባኤ በንባብ ያዳመጠውንና ለውይይት የሚሆኑ ነጥቦችን በመያዝ በይደር ያቆየውን ለሦስተኛ ጊዜ ለዓመታት በባለሙያዎች ተጠንቶ የቀረበውን ህገ ቤተክርስቲያን መርምሮ ጥልቅ ውይይት ካደረገበት በኋላ አስፈላጊውን ማሻሻያ በማድረግ አጽድቆታል።ተሻሽሎ የጸደቀው ህገ ቤተክርስቲያን ለዘመኑ የሚመጥንና ለቤተክርስቲያንናችን ሁሉን አቀፍ አገልግሎት መሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ታምኖበታል።
ከዚህ በተጨማሪ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ
የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ድርጅቶች ዘመኑን በሚመጥንና የቤተክርስቲያናችንን አሰራር በሚያቀላጥፍ መልኩ
ተቋማዊ ቁመናቸው ተጠናክሮ ውጤት ማስመዝገብ ይችሉ ዘንድ ራሳቸውን ችለው ሥራቸውን ማከናወን የሚያስችላቸውን ሁኔታ የሚፈጥር ውሳኔ በማስተላለፍ የእለቱን ጉባኤ በስኬት ማጠናቀቁን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል።የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በነገው እለት ስብሰባው የአዲስአበባ ሀገረ ስብከትና የማኅበራት ማደራጃ ደንቦችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages