ምኩራብ ማለት ለአምልኮትና ለትምህርት ለኅብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ነው፡፡
- ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ በእስራኤል ሀገር ብዙ ምኩራቦች ሰለ ነበሩ እየገባ ወንጌልን አስተምሮባቸዋል፡፡
- "ቦአ ኢየሱስ ምኩራብ ከሚለው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሥያሜውን አግኝቷል፡፡
- በምኩራብ ጸሎትና ትምህርት ይፈጸምበታል፡፡ መስዋዕት ግን አይከናወንም፡፡
- በዚህ ሳምንት ጌታ ቤተ መቅደሱን የገበያ ማዕከል አድርገው፤ ሸቀጥ ዘርግተው፤ በጉን፤ ላሙን፤ ርግቡን እየሸጡ አገኛቸው፡፡ በዚህ
ምክንያት ከምኩራብ አስወጥቶ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የሽፍቶችና የወንበደሰዎች ዋሻ አደረጋችኃት በማለት ወቅሷቸዋል፡፡(ዮሐ ፪፥፲፮)፤
በቤተክርስቲያናችን በስፋት የሚነገርበትና የምንማርበት ሰንበት ነው።
- ምኩራብ ማለት የፀሎት ቤት ማለት ሲሆን በውስጡም ህግና ነብያት ይነገርባታል፣ይነበብበታል።
- ምኩራብ እና ቤተ መቅደስ የተለያዪ ናቸው። ምኩራብ በኢየሩሳሌም እና ከዛ ውጪ አይሁድ በተበተኑበት ስፍራ ሁሉ ሲሰራ ቤተ መቅደስ ግን ከኢየሩሳሌም ውጪ መስራት አይቻልም ነበር።
- ምኩራብ ህግና ነቢያት ቢነበብበትም መስዋዕት አይቀርብበትም፣ ቤተ መቅደስ ግን መስዋዕት ይቀርብበታል፣በምኩራብ ሁሉም መሰብሰብ ይችላሉ፣አለቆችም አሏቸው፣በቤተ መቅደስ ግን ከሊቀ ካህናቱ ውጪ ሌላ ሰው ሊገባበትም አይችልም፣ ሊቀ ካህናቱ ብቻ ገብቶ ለህዝቡ እና ለራሱ መስዋዕት የሚያቀርብበት ነው።
ታድያ እየሱስ ወዴት ነው የገባው?
- ጌታችን እና መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስትስ የገባው ወደ ቤተ መቅደስ አንደሆነ በአራቱም ወንጌል ተፅፍዋል (ዮሐ 2፥14 ፡ማቴ 21፥12 ፡ ማር 11፥15 ፡ ሉቃ 19፥45)
- ታድያ ጌታ ወደ ምኩራብ መግባቱን ቅዱስ ያሬድ ለምን ዘመረ? ብንል በኢየሩሳሌም ኢዮስያስ ከሰራው ቤተ መቅደስ በኋላ ያለውን ዘሩባቤል የሰራውን መቅደስ ወደ ምኩራብነት አውርደውት ከዛም አሳንሰው የንግድ ቤት አድርገውት ነበር።
➭ስለዚህም ቅዱስ ያሬድ
"ቦአ ኢየሱስ ምኩራብ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት" ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ መግባቱን እና የሃይማኖት ቃል ማስተማሩን ቅዱስ ያሬድ ዘምሯል።
በሌላ ስፍራም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደምኩራቦቻቸው ገብቶ እንዳስተማረ እናገኛለን (ማቴ 4፣23)
በሌላ በኩል ደግሞ በሬዎችን እና በጎችን እርግቦችን ከመቅደስ አስወጥቶ እርሱ መግባቱ የብሉይ ኪዳንን መስዋት ማስወገዱን እና እራሱ አማናዊ የአዲስ ኪዳን መስዋት መሆኑን በማሳየት ነው።
ስለዚህ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስትያን (ቤተ መቅደስ) ክርስቶስ ሙሽራዋ የሆነላት ራሱን አሳልፎ የሰጣት የማትፈርስ እና በሰው እጅ ያልተሰራች መቅደስ ስትሆን ይኃውም የእኛ አካል ሲሆን እግዚአብሔር የማይከብርበትን ነገር ከውስጣችን አስወግደን ለሞተልን ጌታ ዋጋ ለከፈለልን ንጉስ በመፍራትና በፍቅር ለመገዛት ከአንደበት ሳይሆን ከልብ በሆነ ማንነት መቅደስ ሰውነታችንን እንድንጠብቅና እግዚአብሔር እንድናከብረው ነው።
እኛ ታድያ ከዚህ ምን እንማር
- 1ኛ.የምኩራብ እና የቤተ መቅደስ ልዩነትን
- 2ኛ የእግዚአብሔር ቤት የጸሎት ቤተ እንጂ የንግድ እና የአድማ ቤት አለመሆኑን
- 3ኛ.ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ሳይሆን የሚሸጡትን ብቻ እንዳስወጣ ሰራተኞችን ግን እንዳስተማራቸው
- 4ኛ መቅደስ ሰውነታችንን በክብር እንድንጠብቅ እና ጌታ ሲመጣ እንዳያዝንብን
- 5ኛ.የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤን
የጌታችን ትምህርት የተቀበሉና ያመኑ ተባርከዋል እኛስ ቃሉን አንብበን አለፍን? ወይስ ተቀበልን? እራሳችንን እንይ?!እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቃሉ ይስራብን። እግዚአብሔር ሠላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ: ዕረፍት ለሕዝባችን ያድልልን።ክብር ለመድኃኔዓለም ይሁን።
No comments:
Post a Comment