ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ሊያደርግ ነው!! - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, March 14, 2023

ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ሊያደርግ ነው!!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ረቡዕ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ እንደሚካሄድ ገለጸ።
እንደ ኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዘገባ በአዲስ አበባ አቅራቢያና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ አዳራሽ እንዲገኙ ጥሪውን አስተላልፏል።
መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጥሪ ተላልፎ ከሁለት ቀናት በኋላ እንደሚካሄድ የተገለጸው የቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ የጥሪ ምክንያት ምን እንደሆነ አልተገለጸም።

(መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱ ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ:-
1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages