ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ 8 - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Friday, June 16, 2023

ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ 8

 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስምሰኔ ስምንት በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም የታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ ክርስቲያንዋ ቅዳሴ ነው። እርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ጋር ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ ሲመለስ ያፈለቀው የተባረከ መታጠቢያ ነው።
ይህም እንዲህ ነው ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ አለው። ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ።
ሄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት ወደ እስራኤልም አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ አዘዘው። በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት እርሷም እስከ ዛሬ አለች ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ በዛሬዪቱ ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ።
እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages