"ከጥገኝነት ወጥታችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።" - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Tuesday, June 6, 2023

"ከጥገኝነት ወጥታችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

የአቡዳቢ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርቲያን መቃረቢያ ቤት ዛሬ በተመረቀበት ወቅት ቡራኬና ቃለ ምእዳን የሰጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዕለቱ ለተገኙ ምእመናን "ከጥገኝነት ወጥታችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።በምትፈልጉት ጊዜ ከፍታችሁ የምትገቡበት ቤ/ክ ስላገኛችሁ ደስ ብሎናል። ይህንን የሚያህል ስፋት ያለውም አይቼ አላውቅም" ብለዋል።
የመጣነው ጊዜያዊውን ቤተ ክርስቲያን ለመባረክና እናንተ ልጆቻችንን ለመጎብኘት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ወደፊትም ለቀራችሁትም እንደሚሰጧችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ገልጸዋል።
በዕለቱ ሀገረ ስብከቱ ለግንባታ ቦታ መረከብ አስተዋፅዖ የነበራቸውን አካላት ያመሰገነ ሲሆን ለቅዱስነታቸውም ልዩ ልዩ ስጦታዎች ተበርክተዋል።






No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages