የቅኔ ሥነ ጥበብ በኢትዮጵያና የ፷ ዓመቱ ጋዜጠኛ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ተመረቀ!! - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, October 22, 2022

የቅኔ ሥነ ጥበብ በኢትዮጵያና የ፷ ዓመቱ ጋዜጠኛ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ተመረቀ!!

የቅኔ ሥነ ጥበብ በኢትዮጵያና የ፷ ዓመቱ ጋዜጠኛ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የመጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ መጽሐፍ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
በተገኙበት ተመረቀ!!


(ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)
የአንጋፋው የቅኔ ሊቅና የቤተክርስተያን ጋዜጠኛ መ/ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ መጽሐፍ በ፵፩ ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ ላይ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቡራኬ ተመርቆ ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።
የቅኔ ሥነ ጥበብ በኢትዮጵያ እና የ፷ ዓመቱ ጋዜጠኛ በሚል ርእስ የተዘጋጀው ይኸው መጽሐፍ ታላቁ የቤተክርስቲያን ሊቅ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ጀምረውት የነበረ መሆኑም ተገልጿል።
ለንባብ የበቃው መጽሐፍ የደራሲውን አጠቃላይ የሕይወት ጉዞና በተለያዩ ጊዜያት የተቀኟቸው ቅኔያት እንዲሁም ልዩ ልዩ ትምህርታዊ ወጎችንና ገጠመኞችን ያካተተ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱ ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ:-

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages