መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራ እንደሚታወቀው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሆና እየሰራች ትገኛለች፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ቋንቋ ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ክፍል የማስተማሪያ መጻሕፍት ያሳተመችውም ይህችው መምህርት ናት፡፡
ይህን መጽሐፍ የተለየ የሚያደርገው በሀገርም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ቋንቋ ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ክፍል ለሆኑ ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ የማስተማሪያ መጻሕፍት መታተሙ ብቻ ሳይሆን ሴትም መሆኗ ጭምር የተለየ ያደርገዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት እና ሊቃውንት በተገኙበት እየተመረቀ ይገኛል። ሊቃውንቱም ቅኔ አቅርበዋል፤ የማህበረ ቅዱሳን መዘምራንም በመገኘት የበገና መዝሙራትን አቅርበዋል፡፡ መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራ መጽሐፉቱን ለማዘጋጀት 15 ዓመታት እንደፈጀባት ለታዳሚው አስረድታለች፡፡ በተጨማሪም የግ ዕዝ ቋንቋ እስከ 12ተኛው ዘመነ መንግስት ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ እንደነበረ ከገለጸች በኋላ ቋንቋውን እንዳይጠፋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአደራነትም ጭምር ጠብቃ እስከ ዛሬም በቋንቋው እየተገለገለችበት እንደሆነ አስረድታለች፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ግለሰቦች ቋንቋው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ እና የአንድ ማህበረሰብ ብቻ አድርገው በሶሻል ሚዲያ ሲያስተጋቡት ይታያል ይደመጣልም ይህ ግን ልክ እንዳልሆነ አስረድታለች፡፡ ያጣነውን ማንነታችን ለማግኘት ወደ ትናንት መመለስ አለብን ስለዚህ የግ ዕዝ ቋንቋን በታዳጊ ሕጻናትና ወጣቶች ላይ እንዲሰራ ወይም እንዲማሩ ታስቦ የተዘጋጀ መጽሐፍት እንደሆነ አስረድታለች፡፡ በመጽሐፍት ምርቃቱ ላይም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፤ መምህራነ ወንጌል እንዲሁም ዘማርያን ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል። ዕኛም መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራን ልናመሰግናት ይገባል እላለሁ፡፡
No comments:
Post a Comment