ከጌታችን ትንሣኤ በኋላ ያለው ረቡዕ :- አልዓዛር - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Thursday, April 20, 2023

ከጌታችን ትንሣኤ በኋላ ያለው ረቡዕ :- አልዓዛር



ከትንሳኤ በኃላ ያለው 3ኛው ቀን አልዓዛር ተብሎ ተሰይሞል፡፡
☞አልዓዛር
☞በዚህ ዕለት የማርያምና የማርታ ወንድም የሆነው አልዓዛር ከሞተ አራት
ቀን
ሆኖት ሳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት አስነሥቶታል፡፡
☞ለትንሣኤ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡
☞ለአይሁድ የአልዓዛር መነሣት ቅናት ፈጥሮባቸዋል፡፡እርሱ ሁሉ ትንሣኤና
ሕይወት መሆኑን ገልጦ ይህንን ቀን ለአልዓዛር መታሰቢያ ይሆን ዘንድ
አልዓዛር
ተብሎ ተሰይሞ ተስቦ ይውላል፡፡(ዮሐ ፲፩፥1-፵፬)
በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን ።
አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያምና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር። ስለዚህ እኅቶቹ ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሞአል ብለው ወደ እርሱ ላኩ።
ኢየሱስም ሰምቶ፦ ይህ ህመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ። ይህን ተናገረ፤ ከዚህም በኋላ፦ ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ አላቸው። ኢየሱስ በቢታንያ አቅራቢያ ከማርታ ከዚያም ከማርያም ጋር ከተገናኘ በኋላ
ወደ አልዓዛር መቃብር አብረው ሄዱ። መቃብሩ ዋሻ ሲሆን መግቢያው በድንጋይ ተዘግቷል። ኢየሱስ “ድንጋዩን አንሱት” አለ። ማርታ፣ ኢየሱስ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ስላልገባት “ጌታ ሆይ፣ አራት ቀን ስለሆነው አሁን
ይሸታል” አለች። ኢየሱስ ግን “ካመንሽ የአምላክን ክብር ታያለሽ ብዬ አልነገርኩሽም?” አላት።— ዮሐንስ 11:39, 40
ስለዚህ ድንጋዩን አነሱት። ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሰማይ እየተመለከተ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “አባት ሆይ፣ ስለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። እውነት ነው፣ ሁልጊዜ
እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፤ ይህን ያልኩት ግን እዚህ የቆሙት ሰዎች አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ ነው።” ኢየሱስ በሕዝቡ ፊት መጸለዩ፣ ቀጥሎ
ከዚያም በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” አለ። አልዓዛር እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ
ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው። ዮሐንስ 11:41-44
አልዓዛር ማርያም እና ማርታ ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል::
በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደ ነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ
የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደ ነበር ሲነግረን ነው እንጂ::
+ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ
ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::
ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን ።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages