ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ 29 - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, May 6, 2023

ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ 29

 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ሚያዝያ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ዕለት ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሐዋርያ_አርስጦስ አረፈ፣ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አባ_አካክዮስ አረፈ።


ሚያዝያ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ዕለት ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሐዋርያ አርስጦስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከሐዋርያት ጋራ በጽርሐ ጽዮን የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበለ በኋላ በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ተናገረ። ሐዋርያትንም እያገለገለ ከእሳቸው ጋራ ሲሰብክ ብዙ ጊዜ መከራ ተቀበለ።
ከዚያም በኋላ ሐዋርያት መርጠው ለኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ሾሙት። በዚችም አገልግሎት ጥቂት ቆይቶ ብናጥስ በሚባል አገር ላይ ሁለተኛ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት።
በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በውስጥዋ አስተምሮ አንድነትንና ሦስትነትን በማሳወቅ የሰዎቿን ልቡና ብሩህ አደረገ። የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሶ አብያተ ክርስቲያንን ሠራ በክብር ባለቤት በጌታችንም ስም አጸናቸው።
ታላላቅ አስደናቂ ተአምራትን በማድረግ መራራ የሆኑ ውኃዎችን ለውጦ ጣፋጮች አደረጋቸው የደረቁ እንጨቶችንም እንዲያለመልሙና እንዲአፈሩ አደረጋቸው። በደዌ የተጨነቁ ብዙ በሽተኞችንም አዳነ ወደ በጎ እርጅና ደርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። እነሆ ሐዋርያው ጳውሎስ በመልእክቱ አስታውሶታል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
በዚህችም ቀን ንጹሕ ደግ ቅን የሆነ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አባ አካክዮስ አረፈ። ይህንንም ቅዱስ ከሀድያን ብዙ ቀኖች አሠቃዩት እግዚአብሔርም በእጆቹ ብዙ ተአምራትን አደረገ ከዚህም በኋላ በፍቅር አንድነት አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages