የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፤ ስለ ጉባኤው ውሳኔዎች ዝርዝር መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ ! - አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15


በቅርብ የተጻፉ

Post Top Ad

Saturday, June 10, 2023

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፤ ስለ ጉባኤው ውሳኔዎች ዝርዝር መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ !



ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለተከታታይ 5 ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን ስብሰባ በዛሬው ዕለት ማጠናቀቁን ተከትሎ ስለ ሲኖዶሱ ውሳኔዎች በቅዱስነታቸው አቡነ አግናጥዮስ ኤፍሬም ዳግማዊ አማካይነት መግለጫ ሰጥቷል።
የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ከአሥር ዓመታት በላይ በኃይል የተሰወሩት ሊቃነ ጳጳሳት ሞር ጎርጎርዮስ ዩሐና ኢብራሂም እና ፖል ያዚጊ እጣ ፈንታ ምን እንደሆነ በጸሎት ጠይቀዋል።
ቅዱስነታቸው ካለፈው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ጊዜ አንስቶ የተከናወኑትን ዐበይት የቤተ ክርስቲያን ስኬቶችና እድገቶችን በሪፖርት አቅርበዋል ፣ ቅዱስነታቸው ባለፈው የካቲት ወር በቱርክና በሶሪያ የደረሰውን ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥና በጉብኝታቸው ወቅት ያስከተለውን አስፈሪ ሁኔታ መመልከታቸውን ገልጸዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች እየታየ ያለውን የኢኮኖሚ ግሽበት እና የኑሮ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱን በመጥቀስ በተለይ በወጣቶች ዘንድ ስደት እንዲጨምር ይኸው የኑሮ ሁኔታ ምክንያት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ፤ ይህንን ችግር ለማስተካከል ቤተ ክርስቲያኒቱ እያደረገች ያለችውን ጥረት ከግምት በማስገባት ሂደቱን በጥሞና መከታተል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በቤተክርስቲያን ውስጥ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ እና ዘጣቶች የነገ ቤተክርስቲያን ተረካቢዎች በመሆናቸው በሁሉም አህጉረ ስብከት የወጣቶች ፕሮጀክት ተቀርጾ ተግባር ላይ መዋሉ የተገመገመ ሲሆን ለቀጣዩ ሥራ ቅዱስ ሲኖዶሱ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የቤተክርስቲያን ልጆች ከአምላክ የራቁና ሃይማኖትን ከሚዋጉ አስተሳሰቦች በሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች መካከል በክርስትና ሃይማኖታቸው ውስጥ እንዲኖሩ እና በያሉበትም ሃይማኖታዊ ማንነታቸውን እንዲጠብቁ ሲኖዶሱ አሳስቧል ።
የማዕከላዊ አሜሪካ በሀገረ ስብከን በተመለከተ ሦስት ጳጳሳትን በመመደብ የሀገረ ስብከቱ መዋቅር በአዲስ መልክ እንዲደራጅ የወሰነ ሲሆን እነዚህን እና ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እና የሀገራቸውን ጉዳዮች የተመለከቱ ጉዳዮችን በመመርመር ውሳኔ አሳልፏል።
ምንጭ፤ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

No comments:

Post a Comment

Post Bottom Ad

Pages